የአውሮጳ ህብረት እና የኢራን የኒዩክልየር ስምምነት  | ዓለም | DW | 16.05.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የአውሮጳ ህብረት እና የኢራን የኒዩክልየር ስምምነት 

ፈረንሳይ ብሪታንያ ጀርመን የአውሮጳ ህብረት ሩስያ እና ቻይና፣ አሜሪካን ባለፈው ሳምንት የጣለችውን የኢራንን የኒዩክልየር ጦር መሣሪያ ባለቤትነት የሚያግደው ስምምነት ፈራሚዎች ናቸው። ከሳውዲ አረብያ እና ከእሥራኤል በስተቀር የአሜሪካ ወዳጅ እና አጋር የሚባሉትን የአውሮጳ ሀገሮችን ጨምሮ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአሜሪካንን እርምጃ አውግዘዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:57

የአውሮጳ ህብረት እና የኢራን የኒዩክልየር ስምምነት 

የአውሮጳ ህብረት፣የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ውድቅ ያደረገቱን የኢራን የኒዩክልየር ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። ፈረንሳይ ብሪታንያ ጀርመን የአውሮጳ ህብረት ሩስያ እና ቻይና ፣  ዩናይትድ ስቴትስ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የጣለችው ኢራን የኒዩክልየር ጦር መሣሪያ ባለቤት እንዳትሆን የሚያግደው ስምምነት ፈራሚ ናቸው። ከሳውዲ አረብያ እና ከእሥራኤል በስተቀር የአሜሪካ ወዳጅ እና አጋር የሚባሉትን የአውሮጳ ሀገሮችን ጨምሮ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአሜሪካንን እርምጃ አውግዘዋል። የኢራን የኒዩክልየር ስምምነት ፈራሚዎች ትናንት ብራሰልስ ቤልጅየም ውስጥ ተገናኝተው በጉዳዩ ላይ መክረዋል። 
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች