1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዋሽ ወንዝ በአፋር መጠነ ሰፊ ጉዳት እያደረሰ ነው

ረቡዕ፣ መስከረም 6 2013

የአዋሽ ወንዝን አቅጣጫ ያስቀየረው የውኃ ግፊት በአፋር በርካታ ስፍራዎች የሚያደርሰው ጉዳት እስካሁንም አላባራም። በክልሉ ዞን 3 አሚባራ ወረዳ ተተፈናቃይ ዜጎች በቂ የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ እያገኙ እንዳልሆነ ሲገልጹ፤ የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት በበኩሉ የችግሩ መጠን ሰፊ መሆን አቅሜን ተፈታትኗል ነው ያለው።

https://p.dw.com/p/3iZ4D
Äthiopien | Nach starken  Regenfällen und Sturzfluten
ምስል DW/S. Getu

«ለተፈናቀሉት በቂ ርዳታ የደረሰ አይደለም»

የአዋሽ ወንዝን አቅጣጫ ያስቀየረው የውኃ ግፊት በአፋር በርካታ ስፍራዎች የሚያደርሰው ጉዳት እስካሁንም አላባራም። በክልሉ ዞን ሶስት አሚባራ ወረዳ ወንዙን ጥሶ የወጣው ጎርፍ በርካታ ዜጎችን ሲያፈናቅል ለቀሰም የሚቀርብ የሸንኮራ አገዳ እና የጥጥ ምርት ላይም በቢሊዮን ገንዘብ የሚገመት ውድመትን ማስከተሉ ተነግሯል። በክልሉ ከነሐሴ ወር ወዲህ ብቻ በ17 ወረዳ 80 ቀበሌዎች ባጋጠመው ጎርፍ ከ238 ሺህ የሚልቁ ዜጎች በውኃው ሙሌት ጦስ ከቀዬያቸው ለመፈናቀል መገደዳቸውን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ለዶይቼ ቨሌ ተናግሯል። በክልሉ ዞን ሶስት አሚባራ ወረዳ ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎች በቂ የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ እያገኙ እንዳልሆነ ሲገልጹ፤ የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት በበኩሉ የችግሩ መጠን ሰፊ መሆን አቅሜን ተፈታትኗል ነው ያለው። ስዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ስዩም ጌቱ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ