1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሸማጋዮቹ የመጀመርያ ቀን የመቀሌ ዉሎ 

ረቡዕ፣ ሰኔ 10 2012

የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና የትግራይ ክልላዊ መሥተዳድርን ለማስታረቅ ወደ መቀሌ ያመሩት የሐይማኖት መሪዎችና ሽማግሌዎች ዛሬ ከትግራይ መስተዳድር ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሕወሃት አባላትና ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ጋር ተገናኝተዉ መክረዋል።

https://p.dw.com/p/3ds7q
Ethiopian religious leaders met with the head of Tigray regional government Dr. Debretsion Gebremichael
ምስል DW/M. Haileselassie

«የሽምግልና ጉዞው ውጤታማ ነበር» የኃይማኖት ተቋማትና የሃገር ሽማግሌዎች ተወካዮች

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና የሀገር ሽማግሌዎች በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና ትግራይ ክልል መንግስት መካከል ያለው መልካም ያልሆነ ግንኙነት በንግግር እንዲፈታ ጥረት ለማድረግ ዛሬ በመቐለ ከትግራይ ክልል መንግስትና የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡ ከውይይታቸው በኋላ ያነጋገርናቸው የሽማግሌዎቹ ተወካዮች የትግራይ ክልል መንግስት ባለስልጣናት ከፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ጋር ለውይይት ዝግጁ መሆናቸው አረጋግጠውልናል ብለዋል፡፡ የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር አብርሃም ተከስተ በበኩላቸው ተፈጥሮ ያለው ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ችግር ለመፍታት ሁሉን ያሳተፈ ውይይት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖት ተቋማት መሪዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ያካተተው 50 ገደማ የሽማግሌዎች ቡድን ዛሬ ጠዋት መቐለ ደርሶ፣ አሁን ላይ ከትግራይ ክልል መንግስት ባለስልጣናት፣ ህወሓት ከፍተኛ አመራሮች፣ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ተወካዮች እንዲሁም የሲቪክ ማሕበራት አመራሮች ጋር በዝግ መክረዋል፡፡

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ