1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማወዛገቡ

ረቡዕ፣ ጳጉሜን 6 2011

የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ወደ ተግባራዊ ጥናት ሊገባ መኾኑን ዐስታወቀ። እስካሁን የቅድመ ዝግጅቶችን ተግባራት ሲያከናውን እንደቆየ የገለጠው የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ጥናት ማካሄድ የሚጀምረው ከመስከረም 2012 ዓም ጀምሮ እንደኾነ ዐስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3PQC8
Äthiopien Tassew Gebre und Ustaz Abubeker Ahmed
ምስል DW/Solomon Muchie

ኮሚሽኑ ሲቋቋም ጀምሮ ድጋፍ እና ተቃውሞ ገጥሞታል

የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ወደ ተግባራዊ ጥናት ሊገባ መኾኑን ዐስታወቀ። እስካሁን የቅድመ ዝግጅቶችን ተግባራት ሲያከናውን እንደቆየ የገለጠው የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ጥናት ማካሄድ የሚጀምረው ከመስከረም 2012 ዓም ጀምሮ እንደኾነ ዐስታውቋል። ኮሚሽኑ ሲቋቋም ጀምሮ የገጠመው ድጋፍ እና ተቃውሞ አኹን እየተንጸባረቀ ነው። ኮሚሽኑን ያቋቋመው አዋጅ ሲጸድቅ ሕገ-መንግሥታዊ ጥሰት ተፈፅሟል ሲል የከሰሰው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አኹን ተቀባይነት የለውም ብሏል። አንዳችም ጣልቃ የለብኝም ያለው  ኮሚሽኑ፦ «በቀላሉ ዝም ብሎ የማይጣል ጥናት ለማጥናት» ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጧል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ ዝርዝር ዘገባ አለው።

ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ