1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትራምፕ ሊከሰሱ ነው

ማክሰኞ፣ ጥር 4 2013

የምክር ቤቱ አባላት በክሱ ላይ ረቡዕ ድምጻቸውን ይሰጣሉ ተብሏል።ባለ አራት ገጹ የምክር ቤቱ ደብዳቤ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ፣የዩናይትድ ስቴትስን ደህንነትና የመንግሥት ተቋማት እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን ለአደጋ በማጋለጥና ሰላማዊ ሽግግርን በማወክ ይከሳል።ትራምፕ ለሐገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት ዴሞክራሲና ሕገ መንግሥት አስጊ መሆናቸው ተጠቅሷል።

https://p.dw.com/p/3nnMW
USA Washington DC Capitol Ausschreitungen
ምስል DW

ትራምፕ ሊከሰሱ ነው

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤቶች መቀመጫ ካፒቶል ሂል አመጽ በማስነሳት ሊከሰሱ ነው። የአሜሪካን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ክሱን ያቀርባል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። በአሶስየትድ ፕሬስ ዘገባ መሠረት የምክር ቤቱ አባላት በክሱ ላይ ረቡዕ ድምጻቸውን ይሰጣሉ ተብሏል። ባለ አራት ገጹ የምክር ቤቱ ደብዳቤ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ፣ የዩናይትድ ስቴትስን ደህንነትና የመንግሥት ተቋማት እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን ለአደጋ በማጋለጥና ሰላማዊ ሽግግርን በማወክ ይከሳል። ትራምፕ በስልጣን ላይ እንዲቆዩ ከተደረገ አሁንም ለሐገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት ዴሞክራሲ እና ሕገ መንግሥት አስጊ መሆናቸው በደብዳቤው ተጠቅሷል። በትራምፕ ላይ ይመሰረታል ስለሚባለው ክስ የዋሽንግተን ዲሲውን ዘጋቢያችንን አነጋግረናቸዋል።


አበበ ፈለቀ
ኂሩት መለሰ