የአሜሪካን ምክር ቤት የCIA ምርመራ ዘገባ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 1 2007ማስታወቂያ
ዘገባዉ CIA በፕሬዝደንት ጆርጅ ቡሽ የስልጣን ዘመን የሽብር ተጠርጣሪዎችን ይመረምርበት የነበረዉ ስልት አሰቃቂ እንደነበር ሆኖም ሀገሪቱን ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2001ዓ,ም መስከረም ጥቃት ወዲህ ከአደጋ ነፃ ሊያደርግ ያልቻለ መሆኑን በዝርዝር አሳይቷል። ዘገባዉን መርምሮ ያቀረበዉ የምክር ቤቱ የስለላ ጉዳይ ተከታታይ ኮሚቴ እንዳመለከተዉ በርከት ያሉ የሽብር ተግባር ተጠርጣሪዎች ጭካኔ ተፈፅሞባቸዋል፤ የCIA ምስጢራዊ እስርቤቶችም ወደማሰቃያ ስፍራነት ተለዉጠዋል። የአዉሮጳ ኅብረት ዘገባዉ ጭካኔ የተሞላበትና ዉጤት አልባ የሆነዉን የCIAን የምርመራ ስልት ማጋለጡ መርሃግብሩ እንዳልተሳካ አሳይቷል ብሎታል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በበኩላቸዉ የCIAን የምርመራ ስልት አጥብቀዉ ተችተዋል። አንድ የተመድ ልዩ መርማሪ በበኩላቸዉ በቡሽ ዘመነ ስልጣን ድርጊቱ እንዲፈፀም የፈቀዱ ባለስልጣናት ክስ እንዲመሰረትባቸዉ ሃሳብ አቅርበዋል። ዘገባዉ የተለያዩ ወገኖችን ትችት ማስከተሉ እየታየነዉ እዚያዉ አሜሪካን ዉስጥስ መገናኛ ብዙሃንም ሆኑ ዜጎች ምን እያሉ ይሆን? ከዋሽንግተን ዲሲ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋን ቀደም ብዬ በስልክ ጠይቄዋለሁ፤
መክብብ ሸዋ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ