1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአልጄሪያ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ጉብኝት

ሰኞ፣ ሐምሌ 26 2013

የአልጄሪያው ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ራምታን ላማምራ ካለፈው ሐሙስ እስከ ቅዳሜ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት እና አስተዳደር ጉዳይ በሚወዛገቡት ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ጉብኝት ላይ ቆይተዋል። በጉብኝታቸው ከሶስቱ አገራት ውጭ ጉዳይ ምኒስትሮች ባደረጓቸው ውይይቶች የታላቁ የኅዳሴ ግድብ ውዝግብ ተነስቷል።

https://p.dw.com/p/3yRTE
Algerien Mali Waffenruhe in Algier vereinbart Außenminister Ramtane Lamamra
ምስል F. Batiche/AFP/Getty Images

የአልጄሪያ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ጉብኝት

የአልጄሪያው ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ራምታን ላማምራ ካለፈው ሐሙስ እስከ ቅዳሜ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት እና አስተዳደር ጉዳይ በሚወዛገቡት ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ጉብኝት ላይ ቆይተዋል። ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ በአዲስ አበባ ከምክትል ጠቅላይ ምኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ደመቀ መኮንን፣ በኻርቱም ከሱዳን አቻቸው መርየም አል-ሳዲቅ እና በካይሮ ከግብጹ ሳሜሕ ሽኩሪ ባደረጓቸው ውይይቶች ኢትዮጵያ እስካሁን አምስት ቢሊዮን ዶላር ገደማ ያወጣችበት ግድብ ጉዳይ መነሳቱ አልቀረም። 
ራምታን ላማምራ በካይሮ ከሳሜሕ ሽኩሪ ጋር ካደረጉት ውይይት በኋላ የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ግንኙነት በወሳኝ ሒደት ውስጥ እያለፈ መሆኑን ተናግረዋል። አልጄሪያ ሶስቱን አገሮች ለማሸማገል ፍላጎት እንዳላት በይፋ የገለጸችው ነገር የለም። 
አልጄሪያ ሶስቱን አገሮች የማደራደር ኃላፊነት የተጣለበት የአፍሪካ ኅብረት እና በግድቡ ምክንያት በተቀሰቀሰው ውዝግብ ለግብጽ አደላ እየተባለ የሚወቀሰው የአረብ ሊግ አባል ነች። 
ሰለሞን ሙጬ

እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ