1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) 75ኛ ዓመት በዓል

ሐሙስ፣ መጋቢት 26 2016

የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ የተመሠረተበትን 75ኛ ዓመት አባል ሃገራት በተገኙበት ብራስልስ ቤልጂየም ላይ ዛሬ ተከበረ። አባል ሃገራቱ በተሰባሰቡበት በዋናነት የወቅቱ ስጋት ባሉት የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ተነጋግረዋል።

https://p.dw.com/p/4eROC
ኔቶ 75ኛ ዓመት
የሰሜን አትላንቲ ክ የጦር ቃል ኪዳን ኔቶ ከተመሰረተ 75 ዓመት ሞላው።ምስል Janine Schmitz/AA/photothek.de/picture alliance

የ(ኔቶ) 75ኛ ዓመት

እ.እ.እ. ሚያዚያ 4 ቀን 1949 ዓ.ም በ12 የአውሮፓና አሜሪካ አገሮች የተመሰረተው የስሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት - ኔቶ 75ኛ አመት በአል፤ አዲስ የተቀላቀሉትን ፊንላንድናና ስዊድንን ጨምሮ  የ32 አባል መንግሥታት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተገኙበት ዛሬ በብራስልስ የድርጅቱ ዋና ጽሕፈት በተካሄደ ሥነሥርዓት ተክብሯል። በሥነ ሥርዓቱ መክፈቻ፤ የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ ሚስተር  ያንስ ሽቶልተንበርግ ባሰሙት ንግግር፤ እእ በ1949 ዓም በዛሬው ዕለት'12 የአሜሪካና  አውሮፓ አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የዋሽንግተንን መሥራች ሰነድ በመፈረም ድርጅቱን እውን በመግለጽ፤ «ዛሬ በዓለማችን ጠንካራና አይበገሬ የሆነው የስሜን አትላንቲክ ድርጅትኔቶ75ኛ ዓመት የሚከበርበት ዕለት ነው» በማለት የእንኳን ደስ አላችሁ መልክት አስተላልፈዋል።

 

በበዓሉ ላይ የተላለፉ መልዕክቶች

 በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተለያዩ አባል መንግሥታት ሚኒስትሮች ባደረጓቸው ንግግሮች፤ የኔቶ አባልነታቸው ለደህንነታቸውና ነጻነታቸው ዋስትና የሰጣቸው መሆኑን በመግለጽ፤ ለድርጅቱ ታማኝ በመሆን የአባልነት ግዴታቸውን ለመወጣት ቃል ገብተዋል። አብዛኞቹም በንግግራቸው ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት በማውገዝና ጦርነቱ ለአባል ሃገራቱም ስጋት በመሆኑ ከዩክሬን ጎን በመቆም እርዳታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

 

የሚኒስትሮቹ መወያያ የነበረው የ100 ቢሊዮን ዩሮ የዕርዳታ ዕቅድ

 የአባል ሃገራቱ ሚኒስትሮች በትናንትና እና ዛሬ ስብሰባቸው፤ ዋና አጀንዳ የነበረው፤ ሩሲያ፤ ክዩክሬን አልፎ በምራቡ ዓለም ላይ ፈጥራለች ያሉት ስጋት እንዲገታና ሰላም እንዲረጋገጥ፤ አባል አገሮችና ኔቶም እንደድርጅት ሊያበረክቱት በሚገባው ተሳፎና አስተዋጾ ላይ ነበር። የሩሲያና ዩኪሬን ጦርነት ከሁለት ዓመት በፊት ከተጀመረ ወዲህ፤ ኔቶና  ብዙዎቹ አባል የሆኑበት የአውሮፓ ሕብረት በቢሊዮን የሚቆጠር የገንዘብና የመሳሪያ ድጋፍ ያደረጉ ቢሆንም፤ ጦርነቱ ግን ዩክሬንን ከማውደም ባለፈ ሩሲያን ከዩኪሬን ግዛት ማሰውጣት እንዳላስቻለ እየተገለጸ ነው።

የዩኪሬን ፕሪዝደንት ቮሌድሚር ዘለንሲኪም፤ አስፈላጊ የሆኑ የጦር መሳሪያዎችና ገንዘብ ባስቸኳይ ካልተላከላቸው፤ ሩሲያኖች ይልቁንም ሊስፋፉና ብዙ ቦታዎችንም ሊይዙ እንደሚችሉ በመግለጽ ጥሪ ማቅረባቸው ተሰምቷል። ሁሉም የኔቶ አባል አገሮች፤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ቢያወግዙም፤ ለዩክሬን የሚሰጡት ድጋፍ ግን እኩል እንዳልሆነ ነው የሚታወቀው። ዋና ጸሐፊ ሽቶልተንበር በጋዜጣዊ መግለጫቸው ዩክሬን በአሁኑ ወቅት የወታደር ሳይሆን የመሳሪያ እጥረት ያጋጥማት መሆኑን በመግለጽ ቀጣይነት ያለው እርዳታ እንደሚያስፈልግ ነበር የገለጹት። «ዩክሪኖች ያጡት ብርታትና ጀግንነት ሳይሆን የጦር መሳሪያና ተተኳሽ ነው፡» በማለትም ሚስትሮቹ  በዋናነት በዚህ ላይ መምከራቸውን አስታውቀዋል።

ኔቶ 75ኛ ዓመት
የኔቶን 75ኛ ዓመት ለማክበር አባል ሃገራት ብራስልስ ቤልጅየም ተሰብስበዋ።e ምስል Geert Vanden Wijngaert/AP Photo/picture alliance

በዚህ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ያተኮሩት፤ ዋና ጸሐፊው ባቀረቡት የ100 ቢዮሊዮን ዩሮ የእርዳታ ዕቅድ ላይ ነውም ተብሏል። ዕቅዱ ቢያንስ ለአምስት ዓመት ለዩክሬን የ100 ቢሊዮን ዩሮ ርዳታ ታቅዶና ታስቦ ባስተማማኝ ሁኔታ የሚደርስበትን ስልት የያዘ ነው ተብሏል። ዋና ጸሐፊ ሽቶልተንበርግ ለዩክሬን የሚሰጠው ድጋፍና እርዳታ ከወትሮው ርዳታ መለውጥ እንዳለበት እንደሚያምኑም አስታውቀዋል።» የምንሰጠውን ድጋፍና ስልቱንም መለወጥ ይኖርብናል ። ርዳታችን አስተማማኛና ቀጣይነት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል በማለት በፈቃደኘት ብቻ ሳይሆን ግዴታም ያለበት መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

 

አዲስ የርዳታ ስልት ያስፈልገበት ምክንያትና ድጋፍና ተቃውሞው

 ከአሜሪካ ይገኛል ተብሎ የታሰበው ተጨማሪ 60 ቢሊዮን ዶላር በምክርቤቱ ቤቱ ስምምነት ማጣት ምክንያት ታግዶ መቆየቱ ብቻ ሳይሆን፤ ብዙም በኔቶ እምነት የላቸውም የሚባሉት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሚስተር ትራምፕ በሚቀጥለው ምርጫ ወደ ሥልጣን ከመጡ፤ የአሜሪካው ድጋፍ ባይነጥፍም ሊቀንስ ስለሚችል፤ የዋና ጸሐፊው እቅድ፤ ይህ እንዳይሆን ለመዘጋጀትና አባል አገሮችን ግዴታ ውስጥ ለማስገባት ታስቦ የቀረበ እንደሆነ ታዛቢዎች ይናገራሉ። አንድንዶቹ አባል መንግሥታት ከወዲሁ ዕቅዱን የደገፉት ሲሆን፤ ሌሎች ደግሞ የእቅዱን ተግብራዊነት የሚጠራጠሩ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። ለሁሉም ግን ዕቅዱ በመጭው ሐምሌ ወር በዋሺንግተን ዲሲ በመሪዎች ደረጃ በሚከበረው የድርጅቱ 75ኛ ዓመት በዓልና ጉባኤ ላይ ለውይይት እንደሚቀርብ ታውቋል።

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ