1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትናንቱ ምርጫ በምሑራን እይታ ከአማራ ክልል

ማክሰኞ፣ ሰኔ 15 2013

ትናንት የተካሄደው አገራዊ ምርጫ ውጤት በባህር ዳር ከተማ ምርጫ ጣቢያዎች በአንዳንዶቹ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የተለጠፈ ሲሆን፤ በርካታ መራጭ የነበሩባቸው ጣቢያ አስፈፃሚዎች ደግሞ ቆጠራቸውን እስከ ሌሊቱ 11 ሰዓት ካከናወኑ በኋላ እስከ ጠዋቱ 3 ሰዓት ድረስ ጊዜያዊ ውጤቶቻቸውን ዐሳውቀዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3vN8s
Äthiopien Bahir Dar | Wahlergebnisse
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

እስከ ጠዋቱ 3 ሰዓት ድረስ ጊዜያዊ ውጤቶቻቸውን ዐሳውቀዋል

ትናንት የተካሄደው አገራዊ ምርጫ ውጤት በባህር ዳር ከተማ ምርጫ ጣቢያዎች በአንዳንዶቹ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የተለጠፈ ሲሆን፤ በርካታ መራጭ የነበሩባቸው ጣቢያ አስፈፃሚዎች ደግሞ ቆጠራቸውን እስከ ሌሊቱ 11 ሰዓት ካከናወኑ በኋላ እስከ ጠዋቱ 3 ሰዓት ድረስ ጊዜያዊ ውጤቶቻቸውን ዐሳውቀዋል፡፡ የዘንድረው ምርጫ ታሪካዊና ለኢትዮጵያ ተሳፋ እንደሆነ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁሩ ዶ/ር ዓለማየሁ እርቅይሁን ይናገራሉ፡፡

ለምርጫው ስኬታማነት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነፃ ሆኖ መደራጀቱ አንድ መልካም ነገር እንደሆነ ዶ/ር ዓለማየሁ አስረድተዋል፡፡ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ዶ/ር በእውቀት ድረስ የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ መሆኑን አመልክተው እንደታዳጊ ዲሞክራሲ ችግሮች ካሉ እንኳ ወደሚመለከተው አካል በማቅረብ መፍትሔ ማስገኘት ተገቢ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡
አሁን ጉድለቶችን ለመናገር ጊዜው ገና ነው ያሉት ዶ/ር በእውቀት፣ አጠቃላይ ውጤት ከታወቀ በኋላ ያለውን ገፅታ ተመልክቶ መተንተኑ የተሸለ ይሆና ብለዋል፡፡

በብዙ አካባቢዎች በፀጥታና በሌሎችም ችግሮች ምርጫ ባልተካሄደበት ሁኔታ ምርጫውን ሙሉ ነው ማለት ይቻል ይሆን? ተብለው ተጠየቁት ዶ/ር ዓለማየሁ የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ምርጫን ማራዘሙ ትክክል ነው፡፡ በአማራ ክልል ምርጫ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ከጥቃቅን ችግሮች በስተቀር በሰላም መጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ