የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን
ማክሰኞ፣ መስከረም 14 2017
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አንድ አንድ ወረዳዎች ውስጥ አማፂያን በትንስፖርት እንቀስቃሴ ላይ የጣሉት እገዳ የነዋሪውን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ማወኩን የየአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡ነዋሪዎች እንደሚሉት በዞኑ በሚገኙ የሱሉላ ፍንጫ፣ጃርቴ፣ አበደንጎሮና አሙሩም ወረዳዎች ካለፈዉ መስከረም መጀመሪያ ጀምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት አንድም ተቋርጧል አለያም እጥረት አለ።አንዳድ አካባቢዎች መንገዶች ከተዘጉ ወራት ማስቆጠሩንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
ነዋሪዎች እንደሚሉትበዞኑ የሱሉላ ፍንጫ ወረዳ ውስጥ ከመስከረም 2 ወዲህ ወደ ዞኑ ዋና ከተማ ሻምቡ የሚወሰደው የትራንስፖርት አገልግሎት በእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት አልፎ አልፍ በእጀባ አገልግሎት እንመዲሰጥ ያነጋርናው ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡ በተመሳሳይ በዞኑ ጃርቴ፣አበደንጎሮና አሙሩም ወረዳዎችም የትንስፖርት አገልግሎት ችግር እንዳለ ተነግረዋል፡፡ በተለይም ከአሙሩ ወረዳ ወደ ዞን ከተማ የሚወስደው የመጓጓዣ አገልግሎት ከተቋረጠ ረጅም ጊዜ ቢሆነውም ወደ አጎራባ ምስራቅ ወለጋ ወረዳዎች ጋር የሚያገኘው መንገድም ከተዘጋ ወራት ማስቆጠሩን አንድ የወረዳው ነዋሪ ጠቁመዋል፡፡
ለተራዘመ ጊዜ በጸጥታ ችግር ውስጥ ከቆዩት የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች መካከል አንዱ በሆነው የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የተወሰኑ ወረዳዎች ውስጥ ከዚህ መስከረም ወር መጀመሪያ አንስቶ የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጎሉን ያነጋርናቸው ነዋሪዎች ተናረግዋል፡፡ በዞኑ ሱሉላ ፍነጫ የሚባል ወረዳ ውስጥ ከመስከረም 2 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ወረዳው ከሌላ አካባቢ ጋር የሚያገናኘው የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡን ስሜ አይገለጽ ያሉ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለዶቼቨለ ተናግረዋል፡፡ የመጓጓዥ አገልግሎት አልፎ አልፎ በእጀባ እንደሚሰጥም ጠቁመዋል፡፡ በዚሁ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የሱሉላ ፍንጫ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ሰኝ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርቷል፡፡
በዞኑ አቤ ደንጎሮ ወረዳምእንደዚሁ ባልታወቀ ምክንያት ተሽከርካሪዎች ወደ ተለያዩ ቦታዎች መንቀሳቀስ በመስጋት ስራ ማቆማቸውን ሌላቸው ያነጋገርናቸው አንድ የወረዳው ነዋሪ ተናግረዋል፡፡ በጸጥታ ስጋት ምክንያት የተሟላ አገልግሎት ያልነበረበት ይህ አካባቢ ከቅርብ ገዜ ወዲህ ደግሞ የትራንስፖርት ገደብ ተጽህኖ ማሳደሩን አክለዋል፡፡
‹‹ ሰዎች በእግር 3 እና 4 ቀናት እየሄዱ ነው፡፡ ሰው መጠያየቅ አልቻለም በጣም እየተቸገረ ነው፡፡ መንገድ በመዘጋቱ ኑሮም በጣም እየተወደደ ነው፡፡‹‹
በሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞንአሙሩ ወረዳም እንደዚሁ ወረዳውን ከሌላ አካባቢ ጋር የሚያገናኘው የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ ይገኛል ተብሏል፡፡ በአሙሩ ወረዳ በተደጋጋሚ ከዚህ ቀደም በተከሰቱት ምክንያት አገልግሎቱ ለ2 ዓመት ያህል መቋረጡን የተናገሩት አንድ ነዋሪ ወደ ምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና በመሄድ የህክምና አገልግሎት ህብረተሰቡ ያገኝ እንደነበር አመልክተዋል፡፡ ይህም በአጎራባች ኪረሙ ወረዳ ውስጥ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ጊዳ አያና የሚወሰደው ትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡን ተናግረዋል፡፡
በነዋሪዎች የተነሳውን የትራንስፖርት ችግርን አስመልክቶ ከየወረዳው አስተዳዳሪዎች መረጃ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አልተሳካም፡፡ በአሙሩ ወረዳ የአጋምሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጌታሁን ደሳለው በሰጡን አስተያየት የትራንስፖርት አገልግሎት ከተቋረጠ ረጅም ጊዜ መሆኑን አንስተዋል፡፡
‹‹ የአጋምሳ ጸጥታው ተሻሽለዋል፡፡ ህዝቡም ወደ ምርት ገብቷል፡፡ የትራንስፖርት አገልግሎት ግን የለንም፡፡ ወደ ዞንም ወደ ወረዳም የለም፡፡ ወደ ወረዳዎች የሚወስድ ትራንስፖርት የለም፡፡‹‹
በሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን ውስጥ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በሰላም እጦት ምክንያት ወደ ለተለያዩ ቦታዎች ተፈነቅለው ነበር የተባሉ በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከወራት በፊት ወደየቤታቸው መመለሳቸውን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በዞኑ የሚስተዋለው የትራንስፖርት አገልግሎት ገደብ በህብረተሰቡ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ተጽህኖ እያሳደረ እንደሚገኝም ተገልጸዋል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
ነጋሽ መሐመድ
ታምራት ዲንሳ