የታጣቂዎች ጥቃት በነጆ ወረዳ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 17 2013ማስታወቂያ
ባለፈው አርብ ሌሊት 10 ሰዓት ገደማ ከቤኒንል ጉሙዝ ከልል ተሻገሩ የተባሉ ታጣቂዎች በምእራብ ወለጋ ነጆ ወረዳ ጥቃት ማድረሳቸውን የነጆ ወረዳ አስተዳደር ዐስታውቋል። በነጆ ወረዳ ያምበልጋራ ኦሊ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ደረሰ በተባለው ጥቃት የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የነጆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታሊላ ተረፋ በስልክ ተናግረዋል። ታጣቂዎቹ በሰው ላይ ካደረሱት ጉዳት በተጨማሪም ቤት ማቃጠላቸውን እና ከብቶችም ዘርፈው መሰወራቸውን አቶ ታሊላ አክለዋል። ፖሊስ ወደ ስፋራው ካቀና በኋላ ከነዋሪው ባገኘው መረጃ መሠረት፦ በነጆ ወረዳ ቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው በቤኒንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በሚገኝና አጎራባች ወረዳ በሆነው ስርባባይ በተባለ ስፍራ ታጣቂዎቹ ሲንቀሰቀሱ እንደነበር ማረጋገጣቸውን አመልክቷል።
ነጋሣ ደሳለኝ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ