የቱሪዝም እና ባህል ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም | ባህል | DW | 27.02.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

የቱሪዝም እና ባህል ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም

ስለየተለያዩ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች አናኗኗር እና ባህል ዘግቧል። ወጣቱ ጋዜጠኛ በኢትዮጵያ ተዘዋውሮ ስላየው ከመዘገብ ባለፈ ፤ከፊል ጉዞውን የሚገልፅ አንድ መፅሀፍም አሳትሟል።

ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የአዲስ አበባ ነዋሪ ነው። ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ እና ህብረተሰቡን እያነጋገረ ብሔረሰቦችን የሚያስተዋውቁ የሬዲዮ ዘገባዎችን አቅርቧል። ሄኖክ በኢትዮጵያ ተዘዋውሮ ያያቸው ቦቻዎች ከሚጠራ ይልቅ፤ ያላየውን ቢቆጥር ይቀለዋል።

የቱሪዝም እና ባህል ጋዜጠኛ ሄኖክ፤ በጉዞው ርካታ የሚሰጠው፤ በሄደበት ቦታ ሁሉ ከተለያዩ ሰዎች ጋር መተዋወቁ እና መቀራረቡ ነው።አንድ የውጭ ሀገር ዜጋ በጉብኝቱ የሚያየውን ጥሩ እና መጥፎ ነገር እንደ ጉዞው አካል ሲቆጥር፤ አንድ ሀገሩን የሚጎበኝ ኢትዮጵያዊ ግን ነገሮችን የሚያይበት እይታ የተለየ ነው ይላል ሄኖክ ።

ብዙ ቦታዎችን የሚጎበኙ ሰዎች ፤ዓለምን በተለየ ዓይን ነው የሚመለከቱት የሚባለውን ሄኖክ ይጋራል። ብዙ ቦታ ማየቱ ፤ ማንነቱን እንዴት እንደለወጠው ሄኖክ ሲናገር፤«የኔ የሆነውን ነገር ብቻ ሳይሆን፤ የሰው የሆነውን ነገር ሁሉ እንዳከብር እና እንድወድ እድል ፈጥሮልኛል» ይላል ። ሄኖክ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ አገር እንዲያይ የስራው ባህሪ እድሉን ቢያሰፋለትም፤ እያንዳንዱ ሰው ይህንን ፍላጎት ሊያዳብር እንደሚገባ ነው ሄኖክ የሚናገረው።

በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎችን የጎነኘው እና ስለ ብሔር ብሔረሰቦች በሬዲዮ ይዘግብ ከነበረው ጋዜጠኛ ሄኖክ ጋር የነበረንን ቆይታ በድምፅ ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic