1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተፈናቃዮቹ የርዳታ ጥያቄ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 20 2015

በአካባቢው ለተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የኦሮሞ ተወላጆች የ”አማራ ታጣቂ” የሚሏቸውን ተጠያቂ ሲያደርጉ፣ ከአመታት በፊት በሰፈራ ፕሮግራም ሄደው በአካባቢዎቹ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ደግሞ የኦሮሚያን መንግስትና ኦነግ ሸኔ የተባለውን ታጣቂ ይከስሳሉ

https://p.dw.com/p/4KF97
Äthiopien Vertriebene aus Wollega in Bahir Dar angekommen | Hauptstadt der Amhara-Region
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በሺ የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ባሕር ዳር ደርሰዋል

                       
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ኪራሙ ወረዳ  በቅርቡ በተደረገዉ ግጭት ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዉ  አማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባሕር ዳር  የደረሱ ተፈናቃዮች አስቸኳይ ርዳታ እንዲሰጣቸዉ ተማፀኑ።ተፈናቃዮቹ እንደሚሉት ለሕይወታቸዉ ከሚያሰጋ ጥቃት ሸሽተዉ ባሕርዳር የደረሱት ከረጅምና አድካሚ እግር ጉዞ በኋላ ነዉ።በተለያዩ የወለጋ ዞኖች በአብዛኛዉ በአማራ ተወላጆች ላይ ባነጣጠረ ተደጋጋሚ  ጥቃት በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል።የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን እንደሚለዉ የሰሞኑን ጥቃት ሸሽተዉ ባሕርዳር ለደረሱ ተፈናቃዮች «አስፈላጊ» ያለዉን ድጋፍ እያደረገ ነዉ።
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን  ኪራሙ ወረዳና በሁሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ በነበሩ የሰላም መደፍረስ በርካታ የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ተገድለዋል፣ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለመፈናቀልና ለከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስ ተዳርገዋል፡፡
በያዝነው ወር መጀመሪያ ሳምንታት ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ በነበረው የሰላም መደፍረስ ከሞት ተርፈው ለሶስት ቀናት ያህል በእግር ተጉዘው አማራ ክልል ከደረሱት የኪራሙና አካባቢው ነዋሪ ተፈናቃዮች መካከል የአንዳንዶቹን አስተያየት ጠይቀናል፡፡
“ወልማይ ትባላለች፣ ቦቃ ቀበሌ ጉደኛ ጂሬና፣ እዛ ነበርን ከዚያ ተፈናቅለን ኪራሙ ገባን፣  ከዚያ ስንኖር አመታችን መስከረም አልፎ በህዳር እንዳሆን አድርገውን ዘመዶቻችን እዛው አልቀዋል፣ ያለቁትም አለቁ የተረፍነውም እነደዚህ ሆነን መጣነ ይኸው ሁለት ሳምንታችን እንጀራ ከበላን ምን ካልነ በዓባይ በረሀ የቀረውም ቀረ መቼም ተቸጋግረን መጣን ወደ ቡሬ ዝም ብለን በጨለማ እየተደናበርን ነው የመጣን (ከመሞት) ይሻለናል ብለን እየተለቃቀስነ፣ እየተዛዘልነ ነው የመጣን” ብለዋል ተፈናቃይዋ፡፡
ከአለፉት 3 ቀናት ጀምሮ  ተፈናቅለው በአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን በር ላይ ከሚገኙት ተፈናቃዮች መካከል 4ሺህ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ባህር ዳር መግባታቸውን ጠቁመው አቅም አጥተው ኪራሙ ለቀሩ ወገኖች መንግስት እንዲደርስላቸው ተማፅነዋል፡፡ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ ከ 50 በላይ ሰዎች ተገደሉ
“ሸኔዎች የልዩ ኃይል በመልበስ እያጭበረበሩ በህብረተሰቡ ገብተው ሁከት በመፍጠር እንዳለ ንብረቱን ሁሉ ትቶ ህዝቡ መጥቷል ማለት ነው፣ የለበሰውን ልብስ ብቻ ለብሶ በበረሀ ኪራሙ 01 ቀበሌ ተነስቶ ዝንጀሮ በማይሄድበት መንገድ ነው ተጉዞ የመጣ፣ አቅም የሌለው እንዳለ ወድቆ ነው የቀረ ደካሞች አዛውንቶች፣ አልመጡም አቅም ያለው ብቻ ነው ለፍቶ እዚህ የደረሰው ከደረሰ በኋላም የተደረገለት ነገር የለም ይኸው ሜዳ ላይ እንደወደቀ ነው ምንም አስተዋፅኦ የለም ከ2000 በላይ ተፈናቃይ ነው፣ እዛ ተከብቦ መውጫ አጥቶ የተቀመጠ አለ መንግስት ይድረስላቸው፡፡”
ኦነግ ሸኔ ባሉት ታጣቂ ቡድን በፈጠረው ችግር በርካታ ውጣ ውረድ አልፈን እዚህ ብንደርስም በቂ እርዳታ አላገኘንም፣ ሲሉ ሌላ ተፈናቃይ አስረድተዋል፡፡
የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ እህታገኘሁ አደመ በርከት ያሉ ተፈናቃዮች ከኦሮሚያ ክልል ኪራሙ ወረዳ መምጣታቸውንና እየመጡም እንደሆነ ጠቁመው አስፈላጊው እገዛም እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
“ከትናንት ወዲያ ጠዋት ጀምሮ በርከት ያለ ቁጥር ያለው ህዝብ ከምስራቅ ወለጋ ኪራሙ ወረዳ ተፈናቅለው እመጡ ነው፣ ከ3 አውቶቡስ በላ የሚሆኑትን ተፈናቃዮች ወደ ፍላቂትና ጃዊ እንዲሁም ወደ ላይ ጋይንት ሸኝተናል ከትናንት ወዲያ ሰፋ ያለ ቁጥር ህዝብ እንደገና የመጣበት ሁኔታ ነው ያለው አሁንም በመንገድ ላይ ያሉ ወደ ክልላችን ያልገቡ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአማራ ተወላጆች እገቡ ነው ምዝገባዎችን አድርገን መኪናዎችን እያመቻቸን ዘመድ ያለው ወደ ዘመዱ፣ ከአንድ ወር ቀለብ ጋር እንሸኛለን የምንችለውን ህል እደረግን ነው፡፡ ” ብለዋል
በአካባቢው ለተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የኦሮሞ ተወላጆች የ”አማራ ታጣቂ” የሚሏቸውን ተጠያቂ ሲያደርጉ፣ ከአመታት በፊት በሰፈራ ፕሮግራም ሄደው በአካባቢዎቹ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ደግሞ የኦሮሚያን መንግስትና ኦነግ ሸኔ የተባለውን ታጣቂ ይከስሳሉየወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች ለተፈናቃዮች ያሰባሰቡት ርዳታ
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ኦነግ ሸኔ ማዕከላዊ አዛዥ የሌለው በመሆኑ ከወታደራዊ እርምጃ ውጪ ሌላ አማራጭ እንዳይወሰድ እንቅፋት ሆኗል በማለት ትናንት በሰጡት መግለጫ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ዓለምነው መኮንን

«ዘመዶቻችን እዛው አልቀዋል» ተፈናቃይዋ
«ዘመዶቻችን እዛው አልቀዋል» ተፈናቃይዋምስል Alemnew Mekonnen/DW
«ዝንጀሮ በማይሄድበት መንገድ ነው ተጉዞ የመጣዉ» ተፈናቃዩ
«ዝንጀሮ በማይሄድበት መንገድ ነው ተጉዞ የመጣዉ» ተፈናቃዩምስል Alemnew Mekonnen/DW

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ