«የባህል አምባሳደር» ስለሺ ደምሴ | ባህል | DW | 03.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

«የባህል አምባሳደር» ስለሺ ደምሴ

የሃገሩ የባህል አንባሳደር፤ በጥበብ የተካነ በሃገሩ በኢትዮጵያ ህዝብና ባህል ማንነት የተቀረፀ፤ ክራር በመደርደር ማንጎራጎር ብቻ ሳይሆን፤ ሃገሩን የሚጠብቅ የሚያስዉብ ሲሉ በሥራዉ ያሞካሹታል፤ ያከብሩታል በሙዚቃዉም የልጅነት ጊዜን ያስታዉሱበታል፤ ይዝናኑበትል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 15:36

ስለሺ ደምሴከአንድ ወር ግድም በፊት ነዉ አርቲስት ስለሺ ደምሴ በጀርመናዉያን ተጋብዞ ኢትዮጵያዉያን ባቀረቡት የስዕል አዉደ-ርዕይ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ ሙዚቃዉን እንዲያቀርብ ተጋብዞ ነዉ እዚሁ ጀርመን ዉስጥ በአጋጣሚ ያገኘነዉ። በዩኤስ አሜሪካ ወደ 30 ዓመት ከኖረ በኋላ ኢትዮጵያ ጠቅልሎ የገባዉ አርቲስት ስለሺ ደምሴ ጀርመንም ቢሆን በየጊዜዉ ሲመላለስ 25 ዓመት እንዳስቆጠረ ነግሮናል። ሙዚቃዎቹ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ባህልን በማሳየቱ ሙዚቃህ ስዕል ነዉ ለሚሉኝ፤ አዎ ስዕል ነዉ ስል እገልፃለሁ ሲል አርቲስት ስለሺ ተናግሮአል። አገር ቤት መድረክ ላይ ከክራሩ ጋር ከሚቀርብበት ይልቅ በተለያዩ የዓለም ሃገራት እየተጋበዘ የሚሄድበት ጊዜ ይበልጣል። በዊጭ ሃገር መድረክም ላይ እየተዘዋወረ ሲያዜም ያምራል ሀገሬ ይላቸዋ፤ ለጋባዦቹ፤ በእንጊሊዘኛም ይተረጉምላቸዋል፤ በፈረንሳይኛም ካስፈልገ ካልሆነ ደግሞ አብረዉ እንዲዘፍኑም ያደርጋል። ታድያ እንዲህ እያለ መድረኩን ታዳሚዉን በመቶ በመቶ ተቆጣጥሮ በኢትዮጵያዉያን ባህላዊ ሙዚቃ ታዳሚዉን ያስደስታል። ምን አይነት ችሎታ ነዉ? ዘዴዉ ምን ይሆን? ስንል ሙዚቀኛ ስለሺ ደምሴን ጠይቀናል። ሙሉዉን ቅንብር ፤ የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመቻን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic