1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምርጫ ዝግጅትና የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ቅሬታ

ሐሙስ፣ ግንቦት 29 2016

የቦሮ ድሞክራሲያዊ ፓርቲ በመተከል ዞን የተለያዩ ቦታዎች ለምርጫ ቅስቀሳ ስራው እንቅፋት እየገጠመው እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ የፓርቲው የውጭና አለም አቀፍ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት ዶር መብራቱ አለሙ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የመሰብሰቢያ አዳራሽ መከልከልን ጨምሮ የፓርቲአቸው አባላት ላይ ወከባና ማስፈራሪዎች እየደረሱ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4gki3
በዞኑ የሚንቀሳቀሰዉ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ግን ጫናና ወከባ እንደሚፈፀምበት አስታዉቀዋል
የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳር የሆኑት አቶ አትንኩት ሽቱ በዞኑ ወከባ የደረሰበት ድርጅት የለም ያሉምስል Negassa Desalegn/DW

የበኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምርጫ ዝግጅትና የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ቅሬታ

 

ሰኔ16/2016 ዓ.ምበቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ምርጫ ቦርድ ዕቅድ ይዟል፡፡ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በክልሉ እያካሄድ ባለው የምርጫ ቅስቀሳ ስራ  ለወከባ እና ለእስር መዳረጉን አስታወቀ፡፡ ፓርቲው አዳራሽ መከልከልን ጨምሮ ብዙ እንግልት እንደደረሰበት ገልጸዋል፡፡ በዞኑ በቡሌን የተባለ ወረዳ ውስጥ አራት አባላቱ እና የምርጫ ወኪሎች ታስሮ እንደነበር የፓርቲው የውጭና ዓለም አቀፍ ጉዳዩች ኃላፊ ዶ/ር መብራቱ አለሙ ተናግረዋል፡፡ ታስሮ ከነበሩት አራት አባላት መካከል ሶስቱ መፈታታቸውን ዛሬ አመልክተዋል፡፡

የመተከል ዞን አስተዳዳር በበኩሉ በምርጫ ሠላማዊ መንገድ እንዲካሄድ ዝግጅት እያረገ እንደሚገኝ ገልጸው በፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ የተደረገ ጫናም ሆነ ማዋከብ የለብም ሲል ገልጸዋል፡፡ ፓርቲው አዳራሽ ተከልከልኩ ብሎ ያቀረበውን ቅሬታ ስህተት መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ ተናግረዋል፡፡

"ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው" ቦሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰኔ 16/20216 ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ማቀዱን ገልጸዋል፡፡ በክልሉ ውስጥ የምንቀሳቀሰው የቦሮ ድሞክራሲያዊ ፓርቲ በመተከል  ዞን የተለያዩ ቦታዎች ለምርጫ ቅስቀሳ ስራው እንቅፋት እየገጠመው እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ የፓርቲው የውጭና አለም አቀፍ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት ዶር መብራቱ አለሙ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የመሰብሰቢያ አዳራሽ መከልከልን ጨምሮ የፓርቲአቸው አባላት ላይ ወከባና ማስፈራሪዎች እየደረሱ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ግንቦት 26/2016 ዓ.ም በመተከል ዞን ቡሌን ወረዳ ውስጥ አራት የፓርቲው አባላትና የምርጫ ወኪሎች ታስሮ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ የፓርቲው አባላት ከምርጫ እንዲወጡና ለማቀደናፍ በተለያዩ የምርጫ ክልሎች ደርሰዋል ያሉትን በደል ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሳወቃቸውን ጠቁመዋል፡፡

መተከል ዞን ዉስጥ የሚንቀሳቀሰዉ ተቃዋሚ ፓርቲ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጫናና ወከባ እንደደረሰበት አስታዉቋል
በኒ ሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር በቅርቡ ምርጫ ከሚደረግባቸዉ አካባቢዎች አንዱ የመተከል ዞን ነዉምስል Negassa Dessakegen/DW

የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳር የሆኑት አቶ አትንኩት ሽቱ የፓርቲውን  ቅሬታ አስመልክቶ በሰቱን ምላሽ በዞኑ ወከባ የደረሰበት ድርጅት የለም ያሉ ሲሆን ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብሏል፡፡ ፓርቲው ተከልከልኩ ያላቸውን አገልግሎቶች አስመልክቶም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ታስሯል ስለተባሉ የቦሮ ድሞክራሲያዊ ፓርቲ አባላትም ለዞኑ አስተዳደር መረጃ እንዳልደረሰው ገልጸዋል፡፡

በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች በምርጫ ቅስቀሳበተመለከተ በፓርቲው ላይ ደርሰዋል የተባለውን እንግልት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ ተቋማት የፓርቲውን ቅሬታ እንዲፈቱ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 27/2016 ለተቋማቱ በላከው ደብዳቤ አመልክቷል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰኔ 16/ 2016 ዓ.ም ይካሄዳል በተባለው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ከስድስት በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ