1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስደተኞች  ጉዳይ ረቂቅ አዋጅ መጽደቅ

ሐሙስ፣ ጥር 9 2011

የስደተኞች  ጉዳይ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 34/2010 አ/ም ዛሬ በዋለው የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት 19ኛ መደበኛ ስብሰባ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡ የእንደራሴው ምክር ቤት አዋጁን ያጸደቀው ከሰፊ ክርክር በኋላ ነው።

https://p.dw.com/p/3Bj3Y
Äthiopien - Parlament
ምስል DW/Y. Gebregziabherረቂቅ አዋጁን ለማሻሻል በተከናወነ የምርመራ ሂደት ስደተኞችን በተመለከተ አሁን እየተፈጠረ ያለውን አለማዊ ፡ አህጉራዊ እና አገራዊ ሁኔታዎችን ማስተናገድ የሚያስችል የህግ ግ ማእቀፍ አስፈላጊ በመሆኑ፡ ኢትዮጵያ ስደተኞችን በማስተናገድ ያላትን መልካም ልምድ አለም የበለጠ እንዲረዳው ፡ ኢትዮጵያዊያን እና ስደተኞች በጋራ የሚሳተፉበት የስራ እድል እንዲፈጠር ያስችላል የሚባለው የስደተኞች ጉዳይ አዋጅ  በሶስት ተቃውሞ እና በአንድ ድምጽ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ከጠንካራ ክርክር በኋላ ጸድቋል፡፡ የእንደራሴው ምክር ቤት አዋጁ ከመጽደቁ በፊት ሰፊ ክርክር ያደረጉ ሲሆን ህጉ ተገቢና የኢትዮጵያን ትክክለኛ ገጥታ የሚጠቅስና የሚወክል ፡ ለሰብአዊነት የተደረገ ጥረት፡ ፖለቲካዊም ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታ ያለው በሚል በአወንታ ሲከራከሩ በሌላ በኩል ስራ አጥነትን የሚያበረታታና ፡ የጸጥታ እና ደህንነት ስጋት የሚያመጣ ስደተኞችን አላግባብ ተጠቃሚሚያደርግ  የሌላ ሃገር ዜጎችን የራስ ዜጋ ለማድረግ አዝማሚያ የታየበት ሲሉ አባላቱ የአዋጁን መጽደቅ አግባብ አለመሆን በማንሳት ተከራክረዋል፡፡ በአዋጁ መሰረት ስደተኞች የሃገሪቱን የፋይናንስ ስርአት ተከትለው የባንክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፡ በሰፋፊ የመስኖ እርሻ ልማተት ስራዎች እንዲሳተተፉ እና በየሰባት አመቱ የሚታደስ የሊዝ መሬት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይፈቅድላቸዋል፡፡ከዚህም ባሻገር በኢንዱስትሪ ፓርኮች ተቀጥረው እንዲሰሩ የሚያግዛቸው መሆኑም ታውቋል፡፡
ሰለሞን ሙጬ
አርያም ተክሌ
ተስፋለም ወልደየስ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ