የስኮትላንድ ሕዝበ ዉሳኔ እና እንደምታዉ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 19.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የስኮትላንድ ሕዝበ ዉሳኔ እና እንደምታዉ

የታላቅዋ ብሪታንያ አካል ስኮትላንድ ለመገንጠል፤ ወይም በሕብረቱ ታቅፎ ለመቀጠል፤ በቀረበዉ ጥያቄ መሰረት ትናንት ሕዝበ ዉሳኔ ከተካሄደ በኋላ፤ ስኮትላንድ እንዳትገነጠል የሚፈልገዉ ወገን ማሸነፉ ታዉቋል። በድምፅ ቆጠራዉ መሰረት የስኮትላንድን በብሪታንያ ሕብረት መቆየትን የሚሹት 55,3 በመቶ አብላጫ ድምፅን ሲያገኙ፤

የስኮትላንድን መገንጠል የሚሹት ደግሞ 44,7 በመቶ ድምፅን አግኝተዉ ሽንፈታቸዉን ተቀብለዋል። በሰሜናዊው ጫፍ የብሪታንያ ግዛት አካል ስኮትላንድ፤ እጎአ በ2012 በተደረገ ስምምነት መሠረት፣ ተገንጥላ የራሷን ነጻነት ለማወጅ ወይም ከ 300 ዓመት በላይ ጸንቶ በቆየው ሕብረት፣ ዩናይትድ ኪንግደም ማለትም በብሪታንያ በሕብረት ለመኖር፤ ትናንት ከንጋቱ ጀምሮ ሕዝቡ ድምፁን ሲሰጥ መዋሉ ይታወቃል።

ውጤቱ ግልጽ መሆኑን የተናገሩት የብሪታንያው ጠ/ሚንስትር ዴቪድ ኬምረን፣ የብሪታንያ ግዛቶች በጠቅላላ ለተሻሻለ መጻዔ ዕድል በሕብረት የሚቆሙበት ጊዜው አሁን ነው ማለታቸው ተጠቅሷል።
«የእስኮትላንድ ሕዝብ በግልጽ ቋንቋ ተናግሯል። ውጤቱም ታይቷል። 4 ብሄራትን ያቀፈችው ሃገራችን በአንድነት እንድትቆይ በመወሰናቸው በሚሊዮን እንደሚቆጠሩት ሰዎች ሁሉ እኔም ተደስቼአለሁ። በዘመቻው ወቅት ፤ የብሪታንያን አንድ አካል የሚለይ ሁኔታ ቢፈጠር ከልብ እጅግ እንደማዝን ተናግሬ ነበር። ይህን አባባሌንም ሆነ ስሜቴን፤ በሀገራችን በተለያዩ ማእዝናት ብቻ ሳይሆን በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ብዙዎች ሰዎች የተገነዘቡት ነው፤ ምክንያቱም ባለፉት ጊዜያት በሕብረት ያከናወንነውን ወደፊትም ምን ልንፈጽም እንደምንችል በመታወቁ ነው። እናም አሁን ብሪታንያ በሕብረት ወደደፊት የምትራመድበት ምዕራፍ ነው ። የወደፊቱ ግሥጋሴ አንዱ አካል ፣ ለስኮትላንድ ሚዛናዊ ፣ ፍትኀዊ መርሕ ማስገኘት ፣ እንዲሁም ለኢንግላንድ፤ ዌልስና ሰሜን አየርላንድም ጠቀሚ መመሪያ ማቅረብ ነው።»
ለምርጫ ብቁ ከሁኑት 4,3 ሚሊዮን ገደማ ስኮትላንዳውያን ፣ ከ 85 ከመቶ በላይ የሚሆኑት ትናንት በተካሄደው ውሳኔ ሕዝብ መሳተፋቸው ታውቋል። የአስኮትላንድ ጠ/ሚንስትርና ግዛቲቱ ከብሪታንይ ተነጥላ ነጻነት እንድታውጅ የታገሉት አሌክስ ሳልመንድ ፣ 1,6 ሚሊዮን ለግዛቲቱ ነጻነት ድምፅ በመስጠታቸው ከማመሥገናቸውም በዴሞክራሲ ወግ የአብላጫውን ድምጽ ማክበር ተገቢ ነው ሲሉ አሳስበዋል።


««--እናውቃለን ፤ አይሆንም የሚል ድምፅ በብዙኃኑ ዘንድ እንዳለ! ውሳኔ ሕዝቡ በሁሉም ወገን ስምምነት ተደርጎበት የተከናወነ ነው። የአስኮትላንድ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት ነጻ ሀገር መሆን አለመሻቱን ወስኗል። የሕዝቡን ብይን እቀበላለሁ። ስኮትላንዳውያን በመላ ይህን እንዲያከብሩ ፣ዴሞክራሲያዊ ብይንን እንዲቀበሉ ጥሪ አቀርባለሁ።» የብሪታንያ ህዝብ ትናንት ከተደረገዉ ሕዝበ ዉሳኔ በኋላ ዉጤቱን እንዴት ተቀበለዉ? የድምፅ ዉጤቱ መቀራረቡ ምናልባትም የግዛቱ ሕዝብ መከፋፈልን ያመጣበት ይሆን? ብሪታንያ በስኮትላንድ አንፃር የሚኖራት የወደፊት የፖለቲካዊም ሆነ የኤኮኖሚ እርምጃ ምን ሊመስል ይችላል? በብሪታንያ ለንደን የምትገኘዉን ወኪላችንን ሀና ደምሴን ደዉለን ስለጉዳዩ አነጋግረናት ነበር።
ሀና ደምሴ
አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic