የስራ ህልማችሁ ምን ያህል ከወላጆቻችሁ ጋር ይጣጣማል? | ወጣቶች | DW | 20.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ወጣቶች

የስራ ህልማችሁ ምን ያህል ከወላጆቻችሁ ጋር ይጣጣማል?

የወደፊት እጣ ፈንታችሁን ራሳችሁ ናችሁ የምትወስኑት ወይስ ኃላፊነቱን ለወላጆቻችሁ ትታችሁታል? የስራ ህልማችሁስ ከወላጆቻችሁ ፍላጎት ጋር ምን ያህል ይጣጣማል? በዛሬው #77ከመቶው በተሰኘው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት የምናነሳው ርዕስ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:26

የወደፊት እጣ ፈንታችሁን ራሳችሁ ናችሁ የምትወስኑት ወይስ ኃላፊነቱን ለወላጆቻችሁ ትታችሁታል?

አብዛኛውን ጊዜ የወላጆች የስራ መስክ የልጆቻቸውን እጣ ፈንታ ሊወስን ይችላል። የናይጄራዊቷ ጄን ኤዜኔ ፍላጎት ግን ከወላጆቿ የተለየ ነው። የዶይቸ ቬለዋ  ካትሪን ጌንስለር እንደዘገበችዉ በናይጄሪያዊቱ ወጣት ኖሊውድ የተሰኘዉን የናጄሪያ የፊልም ኢንዱስትሪ ለመቀላቀል የፊልም ትምህርት ቤት ገብታለች።«ተሰጥኦ ተሰጥኦ ነው። ከሌሎች ሰዎች ራስሽን ለየት የሚያደርገው የጥበብ ተሰጥኦሽን እንድትፈትሺ ያደርግሻል። እኔ ደግሞ የመተወን ተሰጥኦ እስካለኝ ድረስ ወደዚህ መምጣት እና የበለጠ ማወቁ አይከፋም ብዬ ወሰንኩ። እና ሙሉ ስራዬ ይሄ እንዲሆን ስለምፈልግ ነው ወደዚህ የመጣሁት።»

Jane Ezinne Ugoji

ናይጄራዊቷ ጄን ኤዜኔ

ጄን የሶስት ወር ስልጠና ነው እየወሰደች የምትገኘው። ምዝገባው እና ስልጠናው 300 የአሜሪካን ዶላር ያወጣል። ለጄን ግን ክፍያው ወይም የመግቢያ ፈተናው አልነበረም ከባዱ ነገር፤ ወላጆቿን ስለፍላጎቷ ማሳመን እንጂ። እንደ በርካታ ወላጆች እናቷ እና አባቷ ልጃቸው ጠበቃ፣ ሀኪም ወይም ኢንጂኒየር ብትሆን ይመርጣሉ።« እናቴ እንኳን ብዙ ትደግፈኝ ነበር። አባቴ ግን የሆነ ያልተመቸው ነገር ነበር። በመጨረሻ ግን ምንም ሊቀይረው የሚችለው ነገር ስላልነበር እሺ ምርጫሽ ከሆነ እደግፍሻለሁ አለ።»

የጄን አባት የልጃቸውን ምርጫ ያልወደዱት ያለ ምክንያት አይደለም። እኢአ በ1990 የፊልም ኢንዱስትሪው ኖሊውድ ፊልም ማቀናበር ሲጀምር ፊልሞቹ ይቀረፁ የነበሩት ውድ ባልሆኑ ሆቴሎች እና በተቻለ መጠን ብዙ ወጪ በማያስወጣ መልኩ ነበር።ተዋንያዎቹም ቢሆን ብዙ አይከፈላቸውም ነበር። ጄን የምትማርበት የሮያል አርትስ አካዳሚ መስራች ኢሜም ኢቦንግ ሚሶዲ ታድያ ኖሊውድ ጥሩ ባልሆነ ስም ቢታወስ አይገርምም ይላሉ።« መጀመሪያ ላይ ማንም ቁም ነገር ያለው ነው ብሎ ያሰበ አልነበረም። ትኩረት የሰጠውም አልነበረም። ያኔ ባንክ እሰራ ነበር እና ስራዬን ትቼ ይህንን ስልጠና ስጀምር ወላጆቼ እብድ ነሽ ወይ ነበር ያሉት። ምክንያቱም ከስነ ጥበብ ብዙ መስራት ይቻላል ያለ አልነበረም። ከጊዜ በኋላ ግን እየተሻሻለ ነው።»

28.09.2009 DW-TV GLOBAL 3000 NOLLYWOOD

የፊልም ኢንዱስትሪው ኖሊውድ ቀረፃ

በመሆኑም የስልጠና ፈላጊው ቁጥር ጨምሯል። መተወን የኑሩ መሰረታቸው እንዲሆን የሚፈልጉትም ወጣቶች በርካታ ናቸው። ከስምንት አመት በፊት መተወን የጀመረው ዴያሚ ኦካንላዎን ከዚያን ጊዜ አንስቶ በርካታ ሽልማቶችን አግኝቷል። በኖሎውድ ዝነኛ ከሚባሉ ተዋንያንም ዛሬ አንዱ ነው።«እውነታው፤ ጥራት ካለው ከጥሩ ስራ ውጪ ሙያሽን ከፍ የሚያደርገው ምንም ነገር የለም። ምክንያቱም ስራሽ በመጨረሻ የት እንደሚደርስ እና ማን እንደሚያየው፣ ማንን እንደሚማረክ እና ኃላም ለሌላ ፕሮጀክት እንደሚደውልልሽ አታውቂም።»

ኖሊውድ በየአመቱ ከ 1500 በላይ ፊልሞች ያቀናብራል። ይህም ከህንዱ ቦሊውድ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ የፊልም ኢንዱስትሪ ያደርገዋል። ፊልሞቹ ናይጄሪያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሀገራትም ለዕይታ ይቀርባሉ። አንዳንዶቹ እንደውም ለፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች ተተርጉመው ይቀርባሉ። የመጀመሪያ የትወና ስራዋን ለምትጠባበቀው ጄን ጠንክራ ለመስራት የሚገፋፋት ሌላም ነገር አለ። ጥሩ ተዋናይ በሆነች ቁጥር የበለጠ በነፃነት ትወስናለች። ምንም እንኳን ትወና የወላጆቿ ምርጫ ባይሆንም  ጄን ወላጆቿን አሳምና ባመነችበት ሙያ መግፋቱን መርጣለች።

 ኢትዮጵያውያን ወጣቶችስ የስራ ፍላጎታቸው ምን ያህል ከወላጆቻቸው ጋር ይጣጣማል?

የ 24 ዓመቱ ሀቢብ መሀመድ ሲፍትዌር ኢንጂነሪንግ መማር ነው የሚፈልገው። የእናቱ ፍላጎት ግን ከዚህ የተለየ ነው። ሌላው ተሞክሮውን ያካፈለን ሸጋው «ስራዬ ከወላጆቼ ፍላጎት ጋርም ይሁን ምኞቴ ከነበረው ጋር አይገናኝም ይላል። ወጣት ሰይድ ይማር  የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነው። ወደፊት የፖለቲካ ሳይንስ መማር ይፈልጋል። ከእናቱ ጋር የሚኖረው ወጣት እንደሚለው እናቱ የሚፈልጉት ነጋዴ እንዲሆን ነው። ሌሎች በፌስ ቡክ እና በኃትስዓፕ አስተያየታቸውን የሰጡን ወጣቶችም አስተያየት ምኞታችን ከወላጆቻችን ምርጫ ጋር ብዙም አይጣጣምም የሚል ነው። ምክንያቱ ምን ይሆን? በአዲስ አበባ ዮንቨርሲቲ የሶሲዮሎጂ ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር የራስወርቅ አድማሱ ምላሽ ሰጥተውናል።

ሙሉውን ዝግጅት በድምፅ ያገኙታል።

ካትሪን ጌንስለር / ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ

 

 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች