1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል

ሐሙስ፣ መጋቢት 5 2016

በአዲስ አበባ በጎዳናና በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ ብሎም ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የተዳረጉ ሴቶችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለው የሴቶች የተሀድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ዛሬ ተመርቋል፡፡ማዕከሉ በዋነኛነት በሴተኛ-አዳሪነት የተሰማሩትን በመቀበል ሙያዊና ስነ ልቦናዊ ድጋፍና ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ ስራ ያሰማራልም ነው የተባለው፡፡

https://p.dw.com/p/4dWST
የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል
የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልምስል Seyoum Getu/DW

የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል

የፕሮጀክቱ ዓላማ

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በቃሊቲ ክፍለ ከተማ 100 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባው ማዕከሉ ከሶስት እስከ ስድስት ወራት በሚቆይ ጊዜ ለተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች የተዳረጉትን ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች አሰልጥኖ ወደ ስራ የሚስገባ ነው ተብሏል፡፡ በማዕከሉ በአንድ ዙር 2000 ሴቶች መግባት እንደሚችሉና በዓመት ደግሞ እስከ 10 ሺህ የሚደርሱትን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ነው የተመላከተው፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይንሸት በሪሁን የፕሮጀክቱ ዓላማ ይህ ነው ይላሉ፡፡

“ለተለያዩ ማህበራዊ ጉዳቶች የተዳረጉትን ሴቶች ቅድሚያ በመስጠት በተለይም በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ፣ የኤች.አይ.ቪ ተጠቂ የሆኑ እና በጎዳና ላይ የሚተዳደሩትን ባጠቃላይም ለምኖ አዳሪ የሚባሉትን ችሮቻቸውን ለመቅረፍ የተቋቋመ ነው” ብለዋል፡፡ኢትዮጵያ፤ አስገድዶ መድፈር የተፈጸመባቸዉ ሴቶች ፍትህን ያገኛሉ?

የማገገሚያ ማዕከሉ የስራ ፈጠራ 

በ11 ወራ ገደማ ተጀምሮ ተጠናቋል የተባለው ይህ ማዕከል የተለያዩ የማገገሚያ ፕሮግራም እንዳሉትም ተነግሯል፡፡ የምክር አገልግሎት፣ የጤና፣ የምግብ ብሎም ክህሎታቸው ልዳብርባቸው የሚችል የተለያዩ የንድፍ እና የተግባር ስልጠና ተጠቃሚም ይሆናሉ ተብሏል፡፡ የስልጠናውም ዓላማ ከተለለያዩ ማህበራዊ ቀውስ እንዲወጡ የሚያስችል የስራ እድልም እንደሚያመቻችላቸው ተጠቁሟል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይንሸት በሪሁን የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ የሚሆኑ ሴቶች የመመልመያ መስፈርትም ይህ ነው ብለዋል፡፡ “የተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖያዊ ችግር ውስጥ ወደቁ ሴቶች የመርሃግብሩ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡የሴቶችን ቀን እያሰብን ለሴቶች ምን ተደርጓል?

ግን ደግሞ የፕሮጀክቱ ዋነኛ ትኩረት በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩትን ሴቶች ህይወት መታደግ ነው” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል
የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልምስል Seyoum Getu/DW

የሰልጣኞች ቆይታ

ኃላፊዋ እንደሚሉት ወደ ማዕከሉ የሚገቡ ሴቶች የቆይታ ጊዜም እንደየጉዳት መጠናቸው እና የሙያ ስልጠናቸው የሚለያይ ሆኖ እስከ ስድስት ወር በሚኖራቸው የማገገሚ እና ስልጠና ቆይታ የተሌያዩ ክህሎቶችን ይዘው ይወጣሉ፡፡ “የነበሩባቸው የስነልቦና ጉዳት የቆይታ ጊዜያቸውን ይወስነዋል፡፡ ከስነልቦና እስከ የተለያዩ የጤና ድጋፍ የሚሻቸው በዚያው ደረጃ ህክምና ተደርጎላቸው በመረጡት በተለያየ የሙያ ዘርፍ ሰልጥነው እንዲወጡ ነው የሚፈለገው” ብለዋል፡፡ሰልጣኞቹ ማዕከሉን ለቀው ከወጡ በኋላ ከተለያዩ የግል ድርጅቶች እና ረጂ ተቋማት ጋር በመሆን የስራ እድል እንዲመቻችላቸው ጥረት ደረጋልም ተብሏል፡፡

የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል
የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልምስል Seyoum Getu/DW

የማዕከሉ ግንባታ ተጠናቆ ተመርቋል

ዛሬ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በይፋ የተመረቀው ፕሮጀክቱ እስካሁን ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ 500 ሴቶችን ተቀብሎ ስራውን መጀመሩም ተነግሯል፡፡በጦርነት ተፈናቅለዉ ችግር ላይ የሚገኙ ሴቶች

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከፕሮጀክቱ መመረቅ ጋር አያይዘው ባስተላለፉት መልእክትም ማዕከሉ ከሚሰጠው የስነ ልቦና ድጋፍ በተጨማሪ በስነ-ውበትና በፀጉር ስራ፣ በከተማ ግብርና፣ በምግብ ዝግጅት፣ በከተማ ውበት አጠባበቅ፣ በኮምፒዩተር ሙያ፣ በሞግዚትነት፣ በመስተንግዶ፣ በኤሌክትሪክና ሸክላ ስራ፣ በእንጨት ስራዎች እና የልብስ ስፌትን በመሳሰሉ ሙያዎች ስልጠና ይሰጣል ብለዋል፡፡

ማዕከሉ ለሰልጣኞቹ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መሰረታዊ መገልገያዎች እንደተሟሉለትም ተጠቁሟል፡፡

ስዩም ጌቱ

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ