ፖሊስ ሥለሞቱት ሰዎች ቁጥር የሚያዉቀዉ ሆስፒታል ደርሰዉ ስለሞቱት ወይም አስከሬናቸዉ ሆስፒታል ስለደረሰ ሟቾች ብቻ ነዉ።በየአካባቢዉ ተገድለዉ የተቀበሩ ሰዎች በፖሊስ ስሌት ዉስጥ አለመካተታቸዉን አዛዡ አስታዉቀዋል
ካለፈዉ ኃምሌ 11 ጀምሮ የሲዳማ ዞንን ባመሰቃቀለዉ ግጭትና ረብሻ በትንሹ 53 ሰዎች መገደላቸዉን የዞኑ ፖሊስ አዛዥ አረጋገጡ።ምክትል ኮማንደር ዳኛቸዉ ደምሴ ዛሬ እንዳስታወቁት ፖሊስ ሥለሞቱት ሰዎች ቁጥር የሚያዉቀዉ ሆስፒታል ደርሰዉ ስለሞቱት ወይም አስከሬናቸዉ ሆስፒታል ስለደረሰ ሟቾች ብቻ ነዉ።በየአካባቢዉ ተገድለዉ የተቀበሩ ሰዎች በፖሊስ ስሌት ዉስጥ አለመካተታቸዉን አዛዡ አስታዉቀዋል።ከሟቾቹ በተጨማሪ 54 ሰዎች መቁሰላቸዉን የፖሊስ አዛዡ አስታዉቀዉ፣ በረብሻዉ የተጠረጠሩ 935 ሰዎች መያዛቸዉን አረጋግጠዋል።በረብሻዉ ፋብሪካዎች፣ የሸቀጥ መደብሮች፣ ሆቴሎች፣ መኖሪያና መስሪያ ቤቶች መዉደማቸዉን፣ ገሚሶቹ መዘረፋቸዉንም ፖሊስ አስታዉቋል።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ