«የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ግዛት አለቀቀም» ዉሚ
ማክሰኞ፣ ጥር 25 2013ማስታወቂያ
በትግራይ ክልል በዘጠና ሁለት የእርዳታ መስጫ ጣቢያዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እየተዳረሰ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። ሆኖም በአንዳንድ ውስን ቦታዎችና ተፈላጊ የቀድሞው የሕወሓት አመራሮች ይኖሩባቸዋል ተብለው በሚገመቱ ሥፍራዎች ላይ የፀጥታ ጉዳይን መነሻ በማድረግ ድጋፎችን ለማድረስ እንቅፋት መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቃል። የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ጉዳይ አሁንም በሰላም እንዲፈታ ኢትዮጵያ ጥረት እያደረገች ቢሆንም የሱዳን ጦር ሠራዊት ግን አሁንም የኢትዮጵያን ድንበር እንደያዘ መሆኑም ሚኒስቴሩ በሳምንታዊ መግለጫው አስታውቃል። በኮሮና ተኅዋሲ ሥጋት ምክንያት በአዲስ አበባ ይደረግ የነበረው የአፍሪቃ ሕብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ በበይነ መረብ እንዲከናወን ውሳኔ ላይ መደረሱም ተገልጿል።
ሰለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ