1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚና ዲፕሎማሲ የበላይነት ከየት ወዴት?

ረቡዕ፣ ግንቦት 28 2016

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የእርሰበርስ ጦርነቱ በብርቱ እየፈተናት የምትገኘው ኢትዮጵያ በርካታ ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ እድሎችን በአንጻራዊነት በተሻለ መረጋጋት ላይ ላለችው ጎረቤት ኬንያ እያስረከበች ነው በሚል የሚሰነዘሩ አስተያየቶች እየጎሉ መጥተዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4gfcf
Addis Ababa City
ምስል Seyoum Getu/DW

በምስራቅ አፍሪቃ አስቸኳይ ርዳታ ካልደረሰ የረሃብ ወደ “አስከፊ አደጋ” ሊቀየር ይችላል

የምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚና ዲፕሎማሲ የበላይነት

ኢትዮጵያ የተለያዩ ጂኦፖሊቲካል አለመረጋጋቶች በሚያናጉት የአፍሪካ ቀንድ እጅግ ተፈላጊ አገር ሆና ቆይታለች፡፡

በተለይም የአፍሪካ መዲና የሆነች ኢትዮጵያ  የአፍሪካ መግቢያ በር ተደርጋ እንደመታየቷ መዲናዋ አዲስ አበባ ሶስተኛዋ የዓለም ዲፕሎማሲ ማዕከል ትሰኛለች፡፡

ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የእርሰበርስ ጦርነቱ በብርቱ እየፈተናት የምትገኘው ኢትዮጵያ በርካታ ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ እድሎችን በአንጻራዊነት በተሻለ መረጋጋት ላይ ላለችው ጎረቤት ኬንያ  እያስረከበች ነው በሚል የሚሰነዘሩ አስተያየቶች እየጎሉ መጥተዋል፡፡

እየጎላ የመጣው የኬንያ የዲፕሎማሲና የፋይንንስ ድጋፎች

የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንተኝ እና በምጣኔ ሀብት ላይ የሚያጠነጥነው ዲመቴ መጽሃፍ ደራሲ አቶ ሸዋፈራሁ ሽታሁን አሁን አሁን በምስራቅ አፍሪካ የኬንያ ተጽእኖ እጎላ በተቃራኒው ግን የኢትዮጵያ ተጽእኖ እየቀነሰ ለመምጣቱ በጉልህ የሚታይ ያሉት ሁኔታዎች ተስተውለዋል፡፡ በተለይም በምዕራቡ ዓለም ፊት የሚታዩ ለዚህ ደግሞ የራሳቸው ማሳያዎች ይኖሩታልም ብለዋል፡፡

የናይሮቢ ከተማ
የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንተኝ እና በምጣኔ ሀብት ላይ የሚያጠነጥነው ዲመቴ መጽሃፍ ደራሲ አቶ ሸዋፈራሁ ሽታሁን አሁን አሁን በምስራቅ አፍሪካ የኬንያ ተጽእኖ እጎላ በተቃራኒው ግን የኢትዮጵያ ተጽእኖ እየቀነሰ ለመምጣቱ በጉልህ የሚታይ ያሉት ሁኔታዎች ተስተውለዋልምስል Stuart Franklin/Getty Images

በአህጉራዊ የቴክኖሎጅ ውድድር ለፍፃሜ የደረሱት ሁለቱ የቴክኖሎጅ ኩባንያዎች

“ኢትዮጵያ በተለይም ከለውጡ ወዲህ በአገር ውስጥ የሚታየው አለመረጋጋት ለፖለቲካዊ አለመረጋጋት ሳይዳርገን አልቀረም የሚሉት” የሚሉት አቶ ሸዋፈራሁ ይህ አለመረጋጋት ወደ ግጭት-ጦርነት በማምራት ክፉኛ ውድመት ማድረሱን አንስተዋል፡፡ ይህ የጦርነት አዙሪት ሊቀረፍ አለመቻሉም የአገሪቱን ተቀባይነት በመቀነሱ ከውጪ ሊገኝ የሚችለውን የዲፕሎማሲ እና ፋይናንስ ድጋፎችን ማሳሳቱ በጉልህ ታይቷልም ነው የሚሉት፡፡ “ምንም እንኳ አገራት የየራሳቸው ነጻነት ብኖራቸውም ይህ ዓለም የሰጥቶ መቀበል-ሉላዊ ዓለም ነው” የሚሉት ባለሙያው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መደማመት የጠፋባትና መረጋጋት የተሳናት ኢትዮጵያ ዓለሙ የሚፈልገውን የዴሞክራሲ እሴቶችን ለማሟላት የተሳካላት አይመስልም ሲሉ ሃሳባቸውን አክለዋልም፡፡ “ሰላምና መረጋጋት፣ ተጠያቂነትና ግልጽነት ማስፈን፣ ሲቪል ነጻነትና ፖለቲካዊ ነጻነት የመቅጠናቸው ጉዳይ ኬንያን ተመራጭ የዲፕሎማሲ እና ፋይናንስ ድጋፎች ተጠቃሚ እንድትሆን ተመራጭ አድርጓታልም” ነው የተባለው፡፡

የኢትዮጵያ የውስጥ ግጭትና የእርስበርስ ጦርነት ተጽእኖ

ኢትጵያ በትሪሊየን ገንዘብ የሚገመት ብዙ ውድምት ባስተናገደችብትና በመቶ ሺዎች ይገመታል የተባለው የሰው ህይወት በተቀጠፈበት ብሎም ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ በተከሰተበት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የአሜሪካ መንግስት ከሰሃራ በታች ላሉ አገራት የሰጠው የአጎኣ እድል መቋረጡ አንዱና ወነኛ የዲፕሎማሲው ዘርፍ መሻከር ማሳያ ተደርጎ ሲነሳ ቆቷል፡፡ አገሪቱ የሰሜን ኢትዮጵያውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ የቋጨውን የፕሪቶሪያውን ግጭት ማቆም ስምምነት ፈርማ ወደ አንጻረዊ መረጋጋት ብትመለስም ብያንስ እስካሁን የነበሩትን የዲፕሎማሲ ክፍተቶችን በመድፈን ወደ አጎአ እድል ተጠቃሚነት አልተመለሰችም፡፡ ኬንያ በአንጻሩ ግን ከአጎአ ዕድል ብቻ በኣመት ከ600 ሚሊየን ዶላር በላይ እንደምታፍስ ይነገራል፡፡ 

 በኢትዮጵያ እና ጎረቤቶቿ ብርቱ ስጋት ያሳዳረው ድርቅ

የፖለቲካል ኢኮኖሚው ተንታኝ አቶ ሸዋፈራሁ ሽታሁን ለዓለም ንግድ ዝውውር እጅግ አስፈላጊ የሆነው የአፍሪካ ቀንድ ቃጠናን መረጋጋት ማስጠበቅ አያላኑ አገራት እንደ ትልቅ የሰጥቶ መቀበል መርህ የሚመለከቱት ነው ይላሉ፡፡ “በአፍሪካ ቀን የዓለማቀፉ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ ይንቀሳቀሳል፡፡ ይህ ቃጠና ሰላም መሆኑ ለዓለማቀፉ ንግድ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ የዓለምን ንግድ በበላይነት የምቆጣጠሩትና የበላይነታቸውን አስጠብቀው ለመሄድ ለሚያልሙት ደግሞ ይህ ጠቃሚቸው ነው፡፡ ኢትዮጵያም ከውጪ አገራ ጋር የምታደርገው ግንኙነት በዓላማ እና በጥቅም ላይ የተመሰረተ መሆኑን ግልጽ ግንዛቤ ሊኖር ይገባል” ብለዋልም፡፡ በተለይም ከዓለማቀፉ የገንዘብ ተቋማት ጀርባ ያለው አበርክቶዋ እጅጉን የሚገዝፈውን የአሜሪካንን ሚና አሳንሶ የማየት አመለካካት ኢትዮጵያ ውስጥ ይታያል የሚሉት ባለሙያው የኢትዮጵያን ተጽእኖ እያሳነሰ የኬንያን ሚና እያጎላ ከመጠው እውነታ  አንዱ ይሄው ነው ብለዋል፡፡ 

የባቡር መጓጓዣ በኬንያ
በአፍሪካ ቀን የዓለማቀፉ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ ይንቀሳቀሳል፡፡ ይህ ቃጠና ሰላም መሆኑ ለዓለማቀፉ ንግድ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ምስል Tony Karumba/AFP

ኬንያ በፀጥታዉ ም/ቤት የተለዋጭ አባልነት መቀመጫ አገኘች

የብሪክስ አባልነት እንደ ስኬት

ዶይቼ ቬለ በዚህ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት አስተያየት ምን ይሆን የሚለውን ለመመልከት በተለይም በኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ሀሳቡን ለማከል ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ግን በተደጋጋሚ እንደሚያነሳው በርካታ የአፍሪካ አገራት ፍላጎታቸውን አሳይተው እንደ ኢትዮጵያ እና ግብጽ ያሉ አገራት ተቀባይነት ያገኙበት የብሪክስ አባልነት ለኢትዮጵያ ተጽኖ መጉላት ማሳያ ነው፡፡ አቶ ሸዋፈራሁ ግን ይህን እንደ ትልቅ ስኬት አይቆጥሩትም፡፡ ምክንያት ሲሉም ኢትዮጵያ ዛሬም ድረስ ከምስራቅ ይልቅ ከምዕራቡ ዓለም የምታገኛቸው ድጋፎች ይጎላሉ፡፡ የዴሞክራሲ ተቋማትን ማጠናከር እና ውስጣዊ ችግሮችን ከሁሉ ቅድሚያ ሰጥቶ መፍታት የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ተጽእኖ ወደ ተፈለገው አቅጣጫ ልመልስ የሚችል አብይ ጉዳይ መሆኑንም በአስተያየታቸው አንስተዋል፡፡

ሥዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሰ