1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምርጫ ቦርድ ውሳኔና የኦነግ ምላሽ

ሰኞ፣ መጋቢት 20 2013

መጋቢት 04 ቀን 2013 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ጉሌሌ በሚገኘው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ዋና ጽህፈት ቤት ጠቅላላ ጉባኤ አደረኩ ያለው የድርጅቱ አመራር ቡድን የጉባኤው ውጤት በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ውድቅ መደረጉን ተቃወመ፡፡

https://p.dw.com/p/3rLdW
Kejela Megersa
ምስል DW/S. Getachew

መጋቢት 04 ቀን 2013 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ጉሌሌ በሚገኘው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ዋና ጽህፈት ቤት ጠቅላላ ጉባኤ አደረኩ ያለው የድርጅቱ አመራር ቡድን የጉባኤው ውጤት በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ውድቅ መደረጉን ተቃወመ፡፡
ቦርዱ በውሳኔው በአዲስ መልክ የተመረጡ አመራሮችንም ሆነ መዋቅሩን ባያፀድቅም በዚያው እንደሚቀጥሉ ከአመራሮቹ አንዱ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአቶ አራርሶ ቢቂላ አመራርነት ተደርጓል ተብሎ የቀረበለትን ጠቅላላ ጉባኤ እውቅና በመንፈግ፤ በዚህ ጉባኤ የተመረጡትን አዲስ አመራሮች እንደ ኦነግ አመራሮች መቀበል እንደማይችል ያሳወቀው ትናንት ባወጣው መግለጫ ነበር፡፡

ስዩም ጌቱ 

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሠ