የምርጫ ቦርድ እና የተቃዋሚዎች ውይይት
ረቡዕ፣ ጥር 29 2011
ማስታወቂያ
የምርጫ ቦርድ እና የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዛሬ ውይይት አከናወኑ። ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ከምርጫ ቦርድ ጋር የተነጋገሩባቸው የስነምግባር ነጥቦች ዐሥር እንደሚደርሱ ተገልጧል። በምርጫ ቦርድ «ቃል ኪዳን» የሚል ስያሜ የተሰጠው የፊርማ ሰነድ፦ «የስነምግባር ደምብ» በሚል እንዲቀየር የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጠይቀዋል። የስነምግባር ደምቡ ውይይት ያስፈለገበት ምክንያት ፓርቲዎች በቀረበው ደንብ መሰረት እንዲመሩ እና ወደፊትም ምርጫ በሚካሄድበት ጊዜ ሰነዱን መሰረት በማድረግ ለማስፈጸም እንዲመች ነው ተብሏል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ