«የሜርክል ዘመን አላበቃም »
ቅዳሜ፣ ኅዳር 29 2011ማስታወቂያ
ሜርክልን እንዲተኩ በአብላጫ ድምፅ የተመረጡት የ56 ዓመትዋን አነግሬት ክራምፕ ካረንባወር ቀደም ብለው ፓርቲውን በፀሐፊነት ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን የሜርክል ቀኝ እጅ መሆናቸው ይነገራል። ለዚህም ይመስላል ሜርክል በሊቀመንበርነትም በመራሂተ መንግሥትነትም መቀጠሉ በቃኝ ብለው ተራውን ለሌሎቹ የፓርቲው አባላት ቢለቁም የክራምፕ ካረንባወር መመረጥ ያው እሳቸው እንዳሉ ያህል ነው የሚል አስተያየት ከፖለቲከኞች እና ከጋዜጠኞች ያስከተለው። የDW ጀርመንኛው ክፍል ባልደረባ የሆነችው ኢንስ ፖል ሜርክል በመራሂተ መንግሥትነት ይቆያሉ ስትል የጻፈውን አስተያየት እና ሃተታ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለው ተርጉሞታል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል/ኢንስ ፖል
ሸዋዬ ለገሠ