የማን መሆኑ ያልታወቀዉ መቃብር
ሐሙስ፣ ነሐሴ 2 2011ማስታወቂያ
የዶቼ ቬለ «DW» ወኪል የንስ ቦርሸር ቦታዉ ላይ ተገኝቶ እንደዘገበዉ በመርከብ ሜዴተራንያን አቋርጠዉ ወደ አዉሮጳ ለመሻገር ያቀዱና በአደጋ የሰመጡ አፍሪቃዉያን ስደተኞች ፤ አስክሪናቸዉ ደቡብ ቱኒዝያ ባሕር ዳርቻ የባህሩ ወጀብ እየተፋቸዉ አስክሬናቸዉ በየጊዜዉ እንደሚገኝ አመልክቶአል። ይህን ሁኔታ በየጊዜዉ ያጋጠመዉ አንድ የቱኒዝያ ዓሣ አስጋሪ የሰዉ ልጅ ክብር ይገባዋል በሚል አስክሬኑን እየሰበሰበ እዝያዉ ባሕር ዳር መቅበር ቢጀምርም ከጊዜ ወደጊዜ ሜዲተራንያን ባሕር ዉስጥ የሚሰጥመዉ የስደተኛ ቁጥር በመጨመሩ ቀብሩን ብቻዉን ማከናወን ለእሱ እጅግ እንደከበደዉ መናገሩን የ«DW» ወኪል የንስ ቦርሸር ዘግቦአል። ከአፍሪቃ ወደ አዉሮፓ ለመሻገር በጀልባ ሜዲተራንያን ላይ ከሚሳፈሩትና ከሰመጡት ዜጎች መካከል አብዛኞቹ የመጡት ከኢትዮጵያና ኤርትራ መሆኑን የተመድ ዘገባ ያመለክታል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ