የማንነት እና የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮች ኮሚሽን
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 11 2011
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማንነት እና የአስተዳደር ወሰን ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን አጸደቀ። አዋጁ በምክር ቤቱ የጸደቀው በአብላጭ ድምፅ፤ በ 33 ተቃውሞ እና አራት ድምፀ ተአቅቦ ነው።
ምስል Yohannes G/Egziabherማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጁ በአብዛኛ ድምፅ ጸደቀ
በስፍራው የተገኘው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር በዘገባው እንዳመለከተው በምክር ቤቱ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ ሰፋ ያለ ክርክር ተካሂዷል። ቀደም ሲልም ምክር ቤቱ የመከላከያ ሠራዊት ረቂቅ አዋጅን በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ