ነጋሽ መሐመድ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 2 2018ቀዳሚዉ ዝግጅት የዓለም ዜና ነዉ።ዜናዉን የሚለጥቀዉ የዜና መፅሔት ዝግጅታችን፣ የመካከለኛዉ ምሥራቅ ጦርነትና የትንሳኤ በዓል በፍጆታ ሸቀጦች ላይ ያስከተለዉን የዋጋ ጭማሪ በሁለት ርዕሶች ይቃኛል።ዜና መፅሔቱ፣ ኢትዮጵያ የአፍሪቃ ሕብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ሊቀመንበር መሆኗ፣ እስራኤል፣ ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን ያወጁት ተኩስ አቁም ለኢትዮጵያ የሚሰጠዉ ትርጉም እና የኢራንና የዩናይትድ ስቴትስ ድርድርን በየተራ ይቃኛል።ሳምንታዊዉ የወጣቶች ዓለም ታይላንድ ዉስጥ ጠቀም ባለ ደሞዝ ትቀጠራላችሁ የተባሉ ኢትዮጵያዉያ የገጠማቸዉን ተቃራኒ እዉነት ይዳስሳል