የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
ዓርብ፣ ሰኔ 25 2013ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መቀሌን ለቅቆ መውጣቱ ከተሰማ ወዲህ በትግራይ ክልል የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ልጆቻቸው የሚማሩ ወላጆች መገናኛ ስልቶች ባለመኖራቸው ዕጣ ፈንታቸው ስጋት ላይ እንደጣላቸው ይናገራሉ። ለዶቼ ቬለ በኢሜይልና በተለያዩ የማኅበራዊ መገናኛ መስመሮች እባካችሁ ስጋታችንን አሰሙልን፤ ሁኔታውንም አጣሩልን የሚሉ መልእክቶችም ይልካሉ። ከማክሰኞ ጀምሮ የስልክ እና ኢንተርኔት ግንኙነት የተቋረጠ ቢሆንም መቀሌ የሚገኘው ዘጋቢያችን ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ ባገኘው የኢንተርኔት መስመር ተጠቅሞ ጥቂት የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ እንዲገልጹለት ጠይቆ ድምጻቸውን ልኮልናል።
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ