የሐረሪ መስተዳድር ሹም ሽር | ኢትዮጵያ | DW | 08.11.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሐረሪ መስተዳድር ሹም ሽር

የቀድሞዉ ርዕሠ መስተዳድር ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡት ከአራት ወር  በፊት ነበር።አዲሱ ርዕሠ መስተዳድር በክልሉ ለረጅም ዓመታት በተለያዩ ኃላፊነቶች ሲያገለግሉ ነበር

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:23

አዲሱ ርዕሠ መስተዳድር የሐረሪ መስተዳድርን ችግር ይፈቱ ይሆን?

የሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባደረገዉ አስቸኳይ ስብሰባ እስከ ዛሬ የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር የነበሩትን አቶ ሙራድ አብዱላሒን ሽሮ በምትካቸዉ አቶ ኦሪዲን በድሪን በርዕሠ-መስተዳድርነት ሾሟል።የቀድሞዉ ርዕሠ መስተዳድር ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡት ከአራት ወር  በፊት ነበር።አዲሱ ርዕሠ መስተዳድር በክልሉ ለረጅም ዓመታት በተለያዩ ኃላፊነቶች ሲያገለግሉ ነበር። ጉዳዩን የተከታተለዉ የድሬዳዋዉ ጋዜጠኛ መሳይ ተክሉ እንደሚለዉ የአዲሱ ርዕሠ መስተዳድር መሾም የተወሳሰበዉን የሐረሪ መስተዳድር ችግር ለማቃለል ይረዳል የሚል ተስፋ አሳድሯል።

መሳይ ተክሉ

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋዓለም ወልደየስ

Audios and videos on the topic