1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የጥገና ሂደት

ሐሙስ፣ መስከረም 7 2013

የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ጥገና መዘግየቱ በአብያተ ክርስቲያናቱ ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን  የአካባቢው ነዋሪዎች ስጋታቸውን እየገለፁ ነው፡፡የሚመለከታቸው አካላት ደግሞ የኮሮና ተሕዋሲ በፈጠረው ችግር ዋና የጥገና ሥራውን ማከናወን እንዳላስቻላቸው ይናገራሉ፣ ሆኖም ሌሎች የጥናት እና አነስተኛ የጥገና ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3icSO
Unesco Äthiopien - Ortodoxe Kirceh Lalibela
ምስል Getty Images/AFP/C. de Souza

የላሊበላ አብያተክርስትያናት ጥገና ዘግይቷል።

የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ጥገና መዘግየቱ በአብያተ ክርስቲያናቱ ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን  የአካባቢው ነዋሪዎች ስጋታቸውን እየገለፁ ነው፡፡የሚመለከታቸው አካላት ደግሞ የኮሮና ተሕዋሲ በፈጠረው ችግር ዋና የጥገና ሥራውን ማከናወን እንዳላስቻላቸው ይናገራሉ፣ ሆኖም ሌሎች የጥናት እና አነስተኛ የጥገና ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ  (ዶ/ር) ግፊትና የተጠናከረ ጥረት የላሊበላ አቢያተ ክርስቲያናት ጥገና በፈረንሳይ መንግሥት ድጋፍ እንደሚከናወን ስምምነት ላይ ተደርሶ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ የላሊበላ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከዚህ በፊት ለአብያተ ክርስቲያናቱ ደህንነት ሲባል በጣሊያን መንግሥት ተገንብተው የነበሩ መጠለያዎች ለቅርሱ አደጋ እየፈጠሩ መሆናቸውን አመልክተው አሁን  በፈረንሳይ መንግሥት በአዲስ መልክ ለማደስ እንቅስቃሴ የተጀመረ ቢሆንም ኮሮና ቫይረስ በፈጠረው ስጋት መሬት ላይ ወረደ የሚታይ የጥገና እንቅስቃሴ እንደሌለ ነው ነዋሪዎቹ በስጋት የሚናገሩት፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ እንደሚሉት «የጥናትና የዲዛይን ሥራዎች እየተሰሩ ነው» ከሚል ወሬ ከመስማታቸው ውጭ መሬት ላይ ምንም የታይ ነገር የለም” ነው ያሉት፡፡ የላሊበላ ከተማ አስተዳደር የባሕል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ መሪጌታ መልካሙ ዓለሙ በስልክ ለዶይቼ ቬለ እንደገለፁት በአብያተ ክርስቲያኑ ላይ ጉልህ የሚታዩ ችግሮች እየተፈጠሩ ነው፡፡ የምሶሶዎቹ አካላት እየተሰነጣጠቁ ነው፣ ከዚህ በፊት ለአብያተ ክርስቲናቱ መጠለያ ተብለው የተሰሩ ማጥበቂያ ብሎኖችና ማያያዣዎች እየላሉና እወዳደቁ ነውም ብለዋል፡፡ የቅርሱን ሁኔታ የሚያጠኑ 10 ካሜራዎች እንደተገጠሙና ግኝታቸው በየወቅቱ ወደ ፈረንሳይ እንደሚላክ ከዋናው ጥገና በፊት የሚሰሩ ሥራዎች እንዳሉና ወደዋናው ሥራ ለመግባት ኮሮና ችግር መደቀኑንም መሪጌታ መልካሙ  አመልክተዋል፡፡በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአርኪዮሎጂና የቅርስ ጥናት መምህርና የኢትዮጵያና ፈረንይ ቅርስ አድን ፕሮጀክት የኢትየጵያ አስተባባሪ ዶ/ር መንግሥቱ ጎበዜ የአብያተ ክርስቲያናቱን ዋናውን ጥገና ላለማስጀመር ሁለት ነገሮች እንቅፋት መሆናቸውን ያብራራሉ፡፡ «አንደኛው የኮሮና ቫይረስ ስጋት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ዋናውን ጥገና ለማካሄድ የተጀመሩ ጥናቶች መጠናቀቅ አለመቻላቸው ናቸው» ብለዋል፡፡ምሁሩ እንደሚሉት ወደፊት በኢትዮጵያ ያሉ ቅርሶችን በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች መጠገን የሚያስችል እንቅስቃሴ መጀመሩንና በዘርፉ የእራስን አቅምና ክህሎት ለማጠናከር እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

 

ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ