የሂና ጥበብ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 19 2011
ማስታወቂያ
ሰአሊ በቡሩሹ የስእል ጥበቡን ያሳያል፤ የሂና ቅርጽ ሰአሊዎች ደግሞ በሰው እጅና እግር ቆዳ ላይ የሳሉትን ጥበብ ያየ በአሳሳል ብልሐቱ እና በውበቱን ሳይደነቅ አይቀርም። ሴቶች የእጅና የእግር ቆዳን ለማሳመር በሂና አይን የሚስቡ ቅርጽ ይሰራሉ። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሰርግ ወቅት የሂና ቅርጽ መሰራት እየተለመደ ነዉ። ሳሚያ ፉአድ የሂና ቅርጽ እጅና እግር ላይ ትስላለች። ስራውን ከጀመረች ሁለት አመት ሆናታል። የሂና ቅርጽ ስራን መተዳደሪያዋ አድርገዋለች። ከዚሁ ስራዋ ጎን የፋርማሲ ትምህርቷንም ትማራለች። ሳሚያ ልዩ ዝግጅት ሲኖርና በሰርግ ወቅት የሂና ቅርጽ የሚያሰሩ ደንበኞች ወደእስዋ እየመጡ አልያም ያሉበት እየሄደች ትሰራለች። በወጣቶች አለም ዝግጅታችን ከዚህቺው የሂና ቅርጽ ስራን ከምትሰራ ወጣት ጋር ያደረግነውን ቆይታ ይኖረናል። ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ።
ነጃት ኢብራሂም
ነጋሽ መሐመድ