1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች

ረቡዕ፣ ሰኔ 7 2015

ነዋሪነቷ በሀዋሳ ከተማ የሆነችው የ17 ዓመቷ አዳጊ ናዝራዊት ከበደ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሰሞኑን በአገር አቀፍ ደረጃ አዘጋጅቶት በነበረው የሰብአዊ መብቶች ምስለ-ችሎት ውድድር አሸናፊ ሆናለች፡፡

https://p.dw.com/p/4SY9q

 በሀዋሳ የኤስ ኦ ኤስ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ናዝራዊት ለአሸናፊነት የበቃችው ከክፍል ጓደኛዋ በረከት ታምራት ጋር በመሆን በህጻናት ችሎት ዙሪያ ባከሄደችው የችሎት ክርክር ነው፡፡ በውጤቱም በአገር አቀፍ ደረጃ አንደኛ በመውጣት ለወከለችው ትምህርት ቤት ዋንጫ እና የምስክር ወረቀት አስገኝታለች፡፡ አዳጊ ሴቶች በአገራችን የሚታየውን የተዛባ ጾታዊ ሥረዓት በመለወጥ ካሰብንበት መድረስ እንችላለን የምትለው ናዝራዊት “ ለዚህ ሁለት ነገሮች ያስፈልጋሉናል፣ እነሱም ውሳኔ እና ጥረት ናቸው“ብላለች፡፡ #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ: ሊሻን ዳኜ
ቪድዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ