1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ኪነ ጥበብአፍሪቃ

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ‘ታሪኳ’ የሴት ሰዓሊያን አውደ ርዕይ

ሥዩም ጌቱ
ረቡዕ፣ መጋቢት 23 2018

የፈረንጆቹ መጋቢት ወር ማርች-08 የሚከበረውን የዓለማቀፍ የሴቶች ቀን በመንተራስ የሴቶች ወር ተብሎም ይጠቀሳል፡፡ ይህንኑን ምክንያት በማድረግ በዘስፔስ ኢትዮጵያ አርት ጋለሪ መስራች እና ዳይሬክተር ፍሬህይወት ደምሴ አነሳሽነት አዲስ አበባ ውስጥ የተዘጋጀው የአርት ጋለሪ አውደ-ርዕይ ለበርካታ ሴት ሰዓሊያን እድል የሰጠ ነበር፡፡

https://p.dw.com/p/5BXEB

ስምንት ሴት ሰዓሊያን ስራዎቻቸውን ይዘው ለሳምንታት ቀርበው ከህዝብ ጋር የመገናኘት እድል ያገኙበት ይህ መድረክ ተምሳሌት ለሚሆኑ ሴቶች እውቅና የመስጠትና እድልም መፍጠር ዓላማን ያነገበ ነበር።
እንደ አዘጋጆች አስተያየት ዘንድሮ ለተከታታይ አራተኛ ዓመት የተዘጋጀው ይህ የስእል አውደ-ርዕይ በቅርቡ መመለስ የሚለው አዲስ መጽሃፍ ያሳተሙትን ብርቱካን ሚዴቅሳን በመዘከር የዚህን ዓመት የዝግጅቱን መታሰቢያነት በሳቸው ስም አካህዷል፡፡
ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴክሳ በዚህ አውደ-ርዕይ ታድመው ልምዳቸውን በማካፈል ከበርካቶች ጋር ፊትለፊት ተዋውቀውበታልም፡፡
#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
 
 
አቅራቢ፤ ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ፤ ሥዩም ጌቱ