ዉይይት፦ የኢትዮጵያ ለዉጥና ነዉጥ | ኢትዮጵያ | DW | 14.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ዉይይት፦ የኢትዮጵያ ለዉጥና ነዉጥ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድና መንግሥታቸዉ ዕለት በዕለት ሕይወት፤ሐብት፤ንብረት የሚያጠፋዉን፣ ሚሊዮኖችን የሚያፈናቅለዉን  ግጭት ማስቆም፣ ሕግና ሥርዓት ማስከበር አንድም አልቻሉም።ሁለትም አልፈለጉም፣ ሰወስትም ትዕግስታቸዉ እስኪያልቅ ስንት ሰዉ ሕይወቱን መገበር እንዳለበት አይታወቅም

አውዲዮውን ያዳምጡ። 29:27

ኢትዮጵያ ወዴት እመራች ነዉ?

ኢትዮጵያ ዉስጥ አምና በዚሕ ወቅት ሚሊዮነ-ሚሊዮናትን ያስፈነደቀዉ የሠላም፣ የዴሞክራሲ፣ የፍትሕ ብልፅግና ተስፋ ዘንድሮ ባመቱ ባጨናገፍ ኮስምኗል።በደስታ፣ ተስፋ ፈንጠዝያዉ ምትክ በአብዛኛ ሐገሪቱ የጎሳ ግጭት፣ግድያ፣ መፈናቀል ጥርጣሬና አለመተማመን ነግሷል።ባለፈዉ አንድ ዓመት በነበረዉ ግጭት-ቁርቁስ የተገደለዉን ሠዉ ብዛት «በሺ የሚቆጠር» ከማለት በስተቀር በትክክል የቆጠረዉ የለም።በተፈናቃዮች ብዛት ግን ፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንደሚሉት፣ ኢትዮጵያ ታሕሳስ ምብቂያ በተጠናቀቀዉ የጎርጎሪያኑ 2018 ከዓለም አንደኛ ሆናለች።እስከ 3 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ ተፈናቅሏል።

በቦታ ወይም ባካባቢ ይገባኛል፣ በሐብትና ሥልጣን ሰበብ የሚቀጣጠለዉ የጎሳ ጠብ፣የታጣቂዎች ዉጊያ ዛሬም ከከሚሴ-እስከ መተሐራ፣ ከአማሮ እስከ አጣዬ እንደቀጠለ ነዉ።ጠብ፣ዉዝግቡ ማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ወደ ስድብ፣ጥላቻ፣ ቅጥፈት-ክሕደት መድረክነት ለዉጧቸዋል።ርዕሠ-ከተማ አዲስ አበባ ሳትቀር «የኔች-አይደለችም» ዱላ ቀረሽ ዉዝግብ ምክንያት ሆናለች።

የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅርብ የሚከታሉ እንደሚሉት አንዳድ አካባቢዎች የየራሳቸዉን «ነፃ መንግስት» የመሠረቱ ይመስላል።አንዳድ ኃይላት በትጥቅም፣

በተከታይ ብዛትም ከመንግሥት እኩል ፈርጥመዋል።ሌሎቹ በየአካባቢዉ ሰዉ ያጋድላሉ።አምና በገቡት የሰላም ዴሞክራሲ ቃል፤ በሰጡት ተስፋና በወሰዱት እርምጃ ምክንያት ከኢትዮጵያዉያንም ከዉጪም ከፍተኛ ድጋፍና አድናቆት ያተረፉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድና መንግሥታቸዉ ዕለት በዕለት ሕይወት፤ሐብት፤ንብረት የሚያጠፋዉን፣ ሚሊዮኖችን የሚያፈናቅለዉን  ግጭት ማስቆም፣ ሕግና ሥርዓት ማስከበር አንድም አልቻሉም።ሁለትም አልፈለጉም፣ ሰወስትም ትዕግስታቸዉ እስኪያልቅ ስንት ሰዉ ሕይወቱን መገበር እንዳለበት አይታወቅም።

የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሒዩማን ራይትስ ዋች የኢትዮጵያ ጉዳይ አጥኚ በቅርቡ በፃፈዉ መጣጥፍ  «ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲ የምታደርገዉ ሽግግር ከአደገኛ ጉድባ ጋር ተላትሟል።» ይላል

።ሽግግሩ እንዳይደናቀፍ የዉጪ ድጋፍ ያሻታልም ባይ ነዉ።ሌሎች የፖለቲካ ተንታኞች ኢትዮጵያ መንታ መንገድ ላይ ናት ይላሉ።የሽግግሩን ሒደት የገጠመዉ እንቅፋት፣ ምክንያቱና መፍትሔዉ የዛሬ ዉይይታችን ትኩረት።ሰወስት እንግዶች አሉን።

ነጋሽ መሐመድ

 

Audios and videos on the topic