1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«አውቄው ቢሆን ኖሮ» ትረካ

Marta Barroso ማርታ ባሮሶ
ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 21 2015

የቶማስ ሞላ ባለቤት የሆነችው ሊያ በአጭር ዓመታት ውስጥ ሶስት ሴት ልጆች ከወለደች በኋላ መልሳ ለማርገዝ ትንሽ ማገገሚያ ጊዜ ፈልጋለች። በሀያዎቹ አጋማሽ የሚገኘው ቶማስ ግን ወንድ ልጅ እንዲኖረው ስለሚፈልግ ባለቤቱ መልሳ እንድታረግዝ ይፈልጋል።

https://p.dw.com/p/4QIhB
Crime Fighters Episode 6 Family Planing
ምስል DW

ታሪኩ የሚከናወነው የቶማስ ሞላ የትውልድ ስፍራ በሆነችው ጎምቢያ ነው። በሀያዎቹ አጋማሽ የሚገኘው ቶማስ  እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ  የቤተሰብ ምጠና ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አያውቅም ነበር።  ስለሆነም ባለቤቱ ሊያ በእርግዝናዎች መካከል ማገገሚያ ጊዜ ለምን እንደምትሻ ፈፅሞ አይረዳም ነበር። ቶሎ ቶሎ ማርገዝ የእናትየዋን እና የፅንሱን ጤንነት አደጋ ላይ ሊጥል ስለመቻሉም አያውቅም ነበር። ቶማስ በአሁኑ ሰዓት ግቢው ውስጥ የሚገኝ አንድ የፓፓያ ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ ቤተሰቡን ስለገጠው ነገር በፀጸት ይገልፃል።

ይህ የወንጀል ተፋላሚዎቹ ትረካ የቤተሰብ ምጣኔን ጥቅም ፣ ሴቶች በአካሎቻቸው ላይ የመወሰን መብት እንዳላቸው እና ወንዶች ከሴቶች ጋር በእኩልነት መኖር እንዳለባቸው ያሳያል። 

ደራሲ: ማርታ ባሮሶ (ሞዛምፒክ)

ተራኪ : አንዱዓለም ተስፋዬ

ትርጉም እና ቅንብር : ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ ዘገባዎች አሳይ