ኮሮና እና ጥብቅ የዝዉዉር ገደብ በጀርመን
ማክሰኞ፣ ጥር 4 2013ማስታወቂያ
በጀርመን የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭትን ለመግታት አዲስ የተጣለዉ ጥብቅ የዝዉዉር ገደብ ከትናንት ከሰኞ ጥር 3 ቀን፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ገቢራዊ ሆኗል። ትምህርት ቤቶች የስፖርት ማዕከላት ቡና እና ምግብ ቤቶች ተዘግተዋል። አንድ ሰዉ አብሮ ከሚኖረዉ የቤተሰብ አባላት ሌላ ማግኘት የሚችለዉ አንድን ሰዉ ብቻ ነዉ። ተማሪዎች በየቤታቸዉ በኢንተርኔት ትምህርታቸዉን ቀጥለዋል። አዲሱ ደንብ ያዘነዉ የጎርጎረሳዉያን ጥር ወር መጨረሻ ድረስ ተፈፃሚ ይሆናል።ደንቡ ይራዘማል የሚል ግምትና አስተያየትም ከወዲሁ እየተሰጠ ነዉ። ጀርመን ዉስጥ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 863 ሰዎች በኮቪድ 19 ሞተዋል።የኮሮና ተሕዋሲ ጀርመን ዉስጥ የገደለዉ ሰዉ ቁጥር ወደ 42 ሺህ ደርሶአል። በተኅዋሲ የተያዘዉ ሰዉ ቁጥር ሁለት ሚሊዮን ተጠግቷል።
አዜብ ታደሰ
ይልማ ኃይለሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ