1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከፍተኛ የነዳጅ አሻጥርና እጥረት በድሬዳዋ ከተማ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 27 2014

የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች በተለይ ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል በነዳጅ እጥረት እና አሻጥር እጅግ እየተማረረ ነው። አብዛኛው በባጃጅ እና በሌሎች ተሽከርካሪዎች ሥራ የዕለት ገቢ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ወይ ሕገወጡን በምሽት ይገዛሉ አለያም እጃቸውን አጣምረው ይቀመጣሉ።

https://p.dw.com/p/49VCv
Äthiopien | Warteschlagne vor Tankstelle in Dire Dawa
ምስል Messay Teklu/DW

ቀን ነዳጅ የለም እያሉ ማታ በኮዳና ጄሪካን ይቸበችባሉ

የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች በተለይ ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል በነዳጅ እጥረት እና አሻጥር እጅግ እየተማረረ ነው። አብዛኛው በባጃጅ እና በሌሎች ተሽከርካሪዎች ሥራ የዕለት ገቢ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ወይ ሕገወጡን በምሽት ይገዛሉ አለያም እጃቸውን አጣምረው ይቀመጣሉ። የነዳጅ ማደያዎች ቀን ነዳጅ የለም እያሉ ማታ በኮዳ እና ጄሪካን በከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ሕገወጥ ችርቸራውን አጧጡፈውታል። ባለፈው ሳምንትም በተመሳሳይ መልኩ በሐዋሳ ከተማ አሽከርካሪዎች፦ አስተዳደሩ በቀን ቤንዚን አልቋል እያሉ በምሽት በበርሜል በሚቸበችቡ ማደያዎች ላይ ቁጥጥር ሊያደርግ ይገባል ሲሉ ድምፃቸውን ያሰሙበትን ዘገባ አስደምጠን ነበር። ተመሳሳይ የእሮሮ ድምፅ ዛሬም ከድሬዳዋ ከተማ ያስተጋባል። 

መሳይ ተክሉ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ