ከፈረንሳይ ወደ ብሪታኒያ ለመሻገር የሚደረግ አደገኛ ጉዞ
እሑድ፣ ጳጉሜን 3 2016ስደተኞች የጫነ ጀልባ በዚህ ሣምንት መጀመሪያ ከሰሜናዊ ፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ ሲጓዝ በደረሰበት አደጋ የ12 ሰዎች ህይወት ቀጥፏል። ከሟቾች መካከል 6 ህፃናት እና አንድ ነፍሰጡር ሴት ይገኙበታል። ከአደጋው ከ50 በላይ ሰዎች ማትረፍ የተቻለ ሲሆን ከሞቱት ሰዎች መካከል አስሩ ሴቶች እንደሆኑ ታውቋል።
እንደ አንድ ምርመራውን በማካሄድ ላይ እንዳለ ተቋም ማስረጃ የሶሪያ ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪ ቡድን እጁ እንዳለበት ታውቋል። ይህ በንዲህ እንዳለ በጎርጎሮሳዊው 2024 ብቻ ወደ 21,000 የሚጠጉ ስደተኞች ቻናሉን ተሻግረው ወደ እንግሊዝ ገብተዋል።
ለመሆኑ ይህ የመተላለፍያ ቻነል አደገኛነቱ እየታወቀ ለምንድነው ስደተኞቹ ወደዚህ ምጣት ያላቆሙት ምንያህልስ አደገኛ ነው? ይህን በተመለከተ ያጋጠማቸውን ፈታኝ ጉዞ እንዴት አእንደተወጡት ስማቸውንመግከጽ ያልፈለጉ ወጣት የሱዳን ስደተኛ ያለፉበትን መከራ እንዲህ ይገልፃሉ።
ለምን 60% ወጣት አፍሪቃውያን መሰደድን መረጡ?
“አብዛኛው ወደ ሱዳን የመጣው ስደተኛ አፍሪካዊ ነው። ሁላችንም በአንድ ጠባብ ክፍል ታጭቀን ነው የምንቀመጠው” የሚሉት ሱዳናዊ “አንዳንድ ጊዜ ስራ እናገኛለን። ነገር ግንፓሊሶች ድንገት ይመጡና ሁላችንንም እስር ቤት ይከቱናል” ሲሉ ተናግረዋል። ፖሊሶች ከ200 እስከ 300 የሊቢያ ገንዘብ እንደሚጠይቁ የገለጹት ስደተኛ “የከፈለ ወዲያው ሲፈታ ያልቻለ አመት ሁለት አመት ሊከርም ይችላል። እጅግ የሚያሳዝን ህይወት ነው እዚያ ያለው” ሲሉ አስረድተዋል።
“እንደ አንድ አፍሪካዊ ወጣት የሚጠበቅብኝን ሁሉ መከራ ከፍየ ነው እዚህ የደረስኩት” የሚሉት የ19 ዓመቱ ሱዳናዊ “ከዚያ እንደምንም ብለን የሚከፈለውን ከፍለን መርከብ በሚያክል ጀልባ ተጠቅጥቀን ወደ አውሮጳ ያሻግሩናል” ሲሉ ጉዞውን ገልጸዋል።
የአዲሱ የአውሮጳ ኅብረት የፍልሰትና የተገን አሰጣጥ ስምምነት ተግዳሮቶች
“አብዛኛዎቹ በዚህ ስራ የተሰማሩት የሶርያ እና የሊብያ ዜጎች ናቸው። በዚህ ጉዞ የሞት እድሉ ድሉ እጅግ የሰፋ ነው” ሲሉ አስረድተዋል። “አንዳንድ ግዜ እንደሰማችሁት በሙሉ ተሳፋሪው ይሞታል። እኔ በጣም እድለኛ ነኝ” የሚሉት ሱዳናዊ ከሊቢያ ጣልያን፤ ከዚያም ፈረንሳይ መግባታቸውን ገልጸዋል። ከፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ የተሻገሩት ስደተኛ “ወደ እንግሊዝ የሚመጣው በትንሽ ጀልባ ነው። አየሩ መጥፎ ካልሆነ በስተቀር ቀላሉ መንገድ ይሄ ነው” ሲሉ አስረድተዋል።
መኮንን ሚካኤል
እሸቴ በቀለ