1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከደብረ ብርሀን ከተማ የተመለሱ ተፈናቃዮች ቅሬታ

ዓርብ፣ መጋቢት 27 2016

በዞኑ ውስጥ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውንና ከዚህ ቀደም የወደሙ ንብረታቸውም አለመጠገኑን ገልጸዋል፡፡ጊምቢም የተወሰኑ ሰዎች ወደ ተጠገኑ ቤቶች መግባታቸውን ነገር ግን ለተፈናቀሉ ዜጎች የእርሻ መሳሪያ አለመሰጠቱንና የተወሰኑት ሰዎች ደግሞ በአንድ ቦታ በዘተጋጀው መጠለያ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡

https://p.dw.com/p/4eT3J
ከአብዛኞቹ የወለጋ ዞኖች የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደየቀያቸዉ መመለስ አልቻሉም
ደብረብርሐን ሠፍረዉ የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ወረዳቸዉ ቢመለሱም እዚያም ከመጠለያ ጣቢያ አልወጡምምስል Negassa Dessalegn/DW

ከደብረ ብርሀን ከተማ የተመለሱ የተፈናቀሉ ሰዎች ቅሬታ

ከምስራቅ ወለጋ ዞንጎቡ ሳዩና ሲቡ ስሬ ወረዳ ተፈናቅለው ደብረብርሀን ቆይቶ የተመለሱ ዜጎች ወደ አካባቢው ቢመለሱም ወደ ገጠር ቤታቸው ገብቶ መስራት አለመቻላቸውን አስታወቁ፡፡ አብዛኛው ሰው የተመለሰው በከተማ አካባቢ በተዘጋጀው ጊዜያዊ መጠለያ ሲሆን ወደ በአካባቢው በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ወደ ገጠራማ ቦታዎች አለመመለሳቸውን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡ በዞኑ ውስጥ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውንና ከዚህ ቀደም የወደሙ ንብረታቸውም አለመጠገኑን ገልጸዋል፡፡ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌም የተወሰኑ ሰዎች ወደ ተጠገኑ ቤቶች መግባታቸውን ነገር ግን ለተፈናቀሉ ዜጎች የእርሻ መሳሪያ አለመሰጠቱንና የተወሰኑት ሰዎች ደግሞ በአንድ ቦታ በዘተጋጀው መጠለያ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡ ወደ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የተመለሱ የተፈናቀሉ ዜጎች  በወሎ አርቡና ጃራ አካባቢ የነበሩ ናቸው፡፡

አርሶ አደሩ ወደ ስራ መግባት አልቻለም

አቶ መጂድ ኢብራህም የምስራቅ ወለጋ ዞን ጎቡ ሰዩ ወረዳ ነዋሪ ሲሆኑ በየካቲት ወር መጀመሪያ 2016 ዓ.ም  ከደብረ ብርሀን ከተመለሱት መካከል ናቸው፡፡ በወረዳው በተዘጋጀው መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ከ150 በላይ ሰዎች እንደሚገኙም የተናገሩት አቶ መጂድ ወደ ወረዳው ከተመለሱት አንድ ወር በላይ ቢያስቆጥሩም ወደ ቀድሞ ቤታቸው አለመመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡ በገጠራማ አካባቢዎች የነበሩ ቤቶች አብዛኞቹ በመውደማቸው በከተማ አቅራቢያ በተዘጋጀው መጠለያ ጣቢያ መቆየታቸውን አመልክተዋል፡፡ አልፎ አልፎ በጸጥታ ሐይሎችና ሸማቂዎች መካከል ግጭቶች እንደሚከሰቱ በመግለጽ አርሶ አደሩ ወደ ገጠራማ ቦታዎች መሄድ እንማይችልም አክለዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ ወደ ወረዳቸዉ ቢመለሱም ወደ ቀያቸዉ መመለስና ማረስ ግን አልቻሉም (ፎቶ ከክምችታችን)
ከወለጋ ተፈናቅለዉ የነበሩ ዜጎች ወደ ቀድሞ ወረዳቸዉ ግምቢ ቶሌ ሲጓዙ (ፎቶ ከክምችታችን)ምስል Negassa Desalegn/DW

በሲቡ ስሬ ወረዳም እንደዚሁ በርካቶች በአንድ ቦታ በተዘጋጀው መጠለያ እንደሚገኙ እና ወደ ግብርና ስራ መግባት እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡ የካቲት 11/2016 ከደብረ ብርሀን ከተማ ወደ ስቡ ስሬ ወረዳ መመለሳቸውን የነገሩን ስሜ አይገለጽ ያሉ ነዋሪ ወደየ ቀበሌዎች አለመመሳቸውን ገልጸው  በወረዳው ማዕከል በተዘጋጀው መጠለያ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ በ2014 ዓ.ም የአርሶ አደሩ በነበረው ግጭት የአርሶ አደሩ ንብረት በመወደሙ በቀድሞ ቤታቸውን በዘላቂነት ለመቋቋም ካሳ እንደሚሹ ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ወለጋ ጊም ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የተወሰኑ ሰዎች ቤት ተጠግኖላቸዋል  

በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በግጭት ወቅት ተጎድቶ የነበሩ ቤቶች በከፈል ተጠግነው የተወሰኑ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቤቱ መግባታቸውን ወደ ቤታቸው የተመለሱ አንድ ነዋሪ ገልጸዋል፡፡ ሌሎች ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በመጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ በዞኑ ቡሳ ጎኖፋ ይሰጣቹሀል ተብሎ ቃል የተገባላቸው የእርሻ መሳርያ ድጋፍ  አስካሁን አልተሰጠንም ብሏል፡

ነዋሪዎቹ ያነሱትን ቅሬታ አስመልክቶ ከምስራቅ ወለጋ ዞን ቡሳ ጎኖፋ/አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት እና ከዞኑ አስተዳደር እና ጸጥታ  ጽ/ቤት ማብራሪያ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት አልተሳካም፡፡ የምዕራብ ወለጋ ዞን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት ወይም ቡሳ ጎኖፋ ኃላፊ ነጻነት አለማየሁ ወደ ዞናቸው ለተመለሱ ዜጎች የእርሻ መሳሪያ በወቅቱ በግብርና ቢሮ በኩል ይቀርባል ብሏል፡፡ የተፈናቀሉ ዜጎች ሙሉ በመሉ ወደ ቀድሞ ቤታቸው ያልገቡት የወደሙ ቤቶች ጥገና ባለማለቁ እንደሆነም ገልጸው ቀደም ሲል በዞኑ አስተዳደር በተጠገኑ ቤቶች በርካቶች መግታቸውን አክለዋል፡፡

ከግምቢ ቶሌ ቀበሌ ከተፈናቃሉት ነዋሪዎች የተወሰኑት ሲመለሱ (ፎቶ ከክምችታችን)
ከግምቢ ቶል ቀበሌ-ወለጋ የተፈናቃሉ ነዋሪዎች ወደ አካባቢያቸዉ ሲደርሱ (ፎቶ ከክምችታችን)ምስል Negassa Desalegn/DW

‹‹የእርሻ መሳሪያ እና የግብርና ግብአቶችን በተመለከተ በቅርቡ ምላሽ ያገኛል፡፡ በወቅቱ እንዲደርሳቸው ይደረጋል፡፡ አርሶ አደሩ ወደ ስራ ገብቶ ራሱን መቻል አለበት የሚል ግንዛቤ አለን፡፡ የመኖርያ ቤትን አስመልክቶ በካምፒ ያሉም አሉ በተጠገኑ ቤቶች እንዲገቡ የተደረጉም አሉ፡፡‹‹ በምስራቅው እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ባለፉት ዓመታት ተከስቶ በነበሩ ግጭቶች ምክንያት በዞኑ ውስጥ ከተፈናቀሉት በተጨማሪ በርካቶች ወደ ሌሎች ክልሎች ተፈናቅለው ቆይተዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ