1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከመቀሌ ስለመልቀቅ የመንግሥት መግለጫ

ረቡዕ፣ ሰኔ 23 2013

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን እና ጄኔራል ባጫ ደበሌ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫከመቀሌ መውጣት ያስፈለገበትን አብራርተዋል። ገበሬው ተረጋግቶ እርሻውን እንዲያርስ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ርዳታ መግባት አልቻለም፤ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ ነው የሚል ስሞታ ሰበብ ላለመኾን መሆኑን መንግሥት ዐስታወቀ።

https://p.dw.com/p/3vpMi
Konflikt in Äthiopien | Redwan Hussein (l) Außenminister und Bacha Debele Generalleutnant Streitkräfte
ምስል Mulugeta Ayene/AP/dpa/picture alliance

የአምባሳደር ሬድዋን ሑሴንና ጄኔራል ባጫ ደበሌ መግለጫ

ከመቀሌ መውጣት ያስፈለገው ገበሬው ተረጋግቶ እርሻውን እንዲያርስ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ርዳታ መግባት አልቻለም፤ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ ነው የሚል ስሞታ ሰበብ ላለመኾን መሆኑን መንግሥት ዐስታወቀ። የውጭ ጉዳይ እና መከላከያ ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ ጁንታ ያሉት ኃይል ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ስጋት አለመኾኑም ከመቀሌ ለመውጣታቸው ምክንያት መኾኑን ጠቅሰዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን እና ጄኔራል ባጫ ደበሌ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንኑ ተናግረዋል። አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን ከመቀሌ ስለ መልቀቅ ፖለቲካዊ አንደምታ፤  ጄኔራል ባጫ ደበሌ ደግሞ ስለ ወታደራዊ አንደምታው አብራርተዋል። ውጊያው መልኩን ቀይሮ ወደ መንደር መውረዱ፤ የመከላከያ ወጪን ሳይጨምር እስካሁን ከአንድ መቶ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መፍሰሱም ተጠቅሷል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሀመድ