1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦነግ በምርጫዉ አይሳተፍም

ዓርብ፣ የካቲት 12 2013

የግንባሩ ሊቀመንበር ዳዉድ ኢብሳ ዛሬ እንዳሉት ግንባራቸዉ በምርጫዉ ሊሳተፍባቸዉ የሚችላቸዉ መንገዶች በሙሉ ተዘግተዉበታል።

https://p.dw.com/p/3pbsB
Äthiopien Treffen Volksgruppe der Oromo Dawud Ibssa
ምስል DW/S. Muchie

«የኦነግ አባላት ታስረዋል፣ ፅሕፈት ቤቶቹ ተዘግተዋልም» አቶ ዳዉድ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በመጪዉ ግንቦት ሊደረግ በታቀደዉ ምርጫ መወዳደር እንደማይችል አስታወቀ።የግንባሩ ሊቀመንበር ዳዉድ ኢብሳ ዛሬ እንዳሉት ግንባራቸዉ በምርጫዉ ሊሳተፍባቸዉ የሚችላቸዉ መንገዶች በሙሉ ተዘግተዉበታል።አቶ ዳዉድ በተለይ ከዶቸ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በየአካባቢዉ የነበሩ የግንባሩ ፅሕፈት ቤቶች ተዘግተዋል፣ባለስልጣናቱና አባላቱ ታሥረዋል ብለዋል።ግንባሩ በምርጫዉ ለመወዳደር ከአምና ጀምሮ ሲዘጋጅ እንደነበረ አቶ ዳዉድ ገልፀዉ አሁን ግን ኦነግ በምርጫዉ እንዳይወዳደር «ተገፍቷል» ይላሉ-ሊቀመንበር ዳዉድ ኢብሳ።

 ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ