1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኑሮን ፈታኝ ደረገው የኦሮሚያ መጓጓዣ ፍሰት እና ተግዳሮቱ

ረቡዕ፣ የካቲት 6 2016

በኦሮሚያ ክልል አለመረጋጋት በሚስተዋልባቸው በተለያዩ አከባቢዎች እና መስመሮቻቸው ምርት እና ሸቀጦችን እንዳሻቸው ማንቀሳቀስ አዳጋች መሆኑ ኑን አዳጋች እንዳደረገባቸው አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ ያጋሩ ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡

https://p.dw.com/p/4cOhS
Ethiopia , Oromia regional state Nekemt city
ምስል Negasa Desalegn/DW

ኑሮን ፈታኝ ደረገው የትራንስፖርት ፍሰት ተግዳሮት

በኦሮሚያ ክልል አለመረጋጋት በሚስተዋልባቸው በተለያዩ አከባቢዎች እና መስመሮቻቸው ምርት እና ሸቀጦችን እንዳሻቸው ማንቀሳቀስ አዳጋች መሆኑን አዳጋች እንዳደረገባቸው አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ ያጋሩ ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡

በቅርቡ በክልሉ በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ አካላት ተጠራ በተባለው የእንቅስቃሴ ገደብ ተስተጓጉሎ የነበረው የመንገደኞች እንቅስቃሴ፤ ገደቡ ከተነሳም በኋላ ጥላው አለመገፈፉን ነው ነዋሪዎች በምሬት የሚናገሩት ፡፡ለኦሮሚያው የጸጥታ ችግር የሦስተኛ ዙር ድርድር እድል

የሰላም ይዞታ

አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ ከሰጡ አስተያየት ሰጪዎች የምስራቅ ወለጋው ኪረሙ ወረዳ ነዋሪ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እኚህ ስሜ አይጠቀስ ብለው ሃሳባቸውን ያጋሩን ነዋሪ አሁን አሁን በአከባቢያቸው “የተረጋጋ የሚመስል” ሰላም ብስተዋልም ዘለቄታው ግን እንደሚሳስባቸው በማስረዳት ነው ሃሳባቸውን የጀመሩት፡፡ “ለጊዜው ምንም አይልም ጸጥ ረጭ እንዳለ ነው፡፡ግን ደግሞ ምን መጣ ሆን የሚለው ያሳስበናል፡፡ በተለይ በጎጃም በኩል ያለው አለመረጋጋት ለኛም ወሰን ላይ ላለነው ስጋት ነው” ብለዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ውስጥ ያለው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ
አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ ከሰጡ አስተያየት ሰጪዎች የምስራቅ ወለጋው ኪረሙ ወረዳ ነዋሪ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እኚህ ስሜ አይጠቀስ ብለው ሃሳባቸውን ያጋሩን ነዋሪ አሁን አሁን በአከባቢያቸው “የተረጋጋ የሚመስል” ሰላም ብስተዋልም ዘለቄታው ግን እንደሚሳስባቸው በማስረዳት ነው ሃሳባቸውን የጀመሩት፡፡ “ለጊዜው ምንም አይልም ጸጥ ረጭ እንዳለ ነው፡፡

የትራንስፖርት እንቅስቃሴው ማነስ በሸቀጦች ዝውውር ላይ ያለው አንድምታ

አስተያየት ሰጪው ወረዳቸውን በሚያዋስነው የጎጃም ቡሬ ወረዳ በመንግስት እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከባድ ያሉት ውጊያ እንደሚካሄድም ነው የጠቆሙት፡፡ አስተያየት ሰጪያችን አክለውም በጸጥታ ስጋት ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አስጊ መሆኑን ተከትሎ ኑሮ ፈትኖአቸዋል፡፡ በተለይም ወደ አከባቢው የሚሄደው ሸቀጣሸቀጥ በአቅርቦት እጥረት እንደፈተናቸውም አስረድተዋል፡፡ “በየቦታው ዝርፊያ ነው፡፡ ሾፌር ይገደደላል፡፡ አንዳንዴ ሸቀጥ በመከላከያ ታጅቦ ይመጣል፡፡ በርግጥ ህዝቡ ተፈናቃይ እንደመሆኑ በእጁ ያለው ወረት አልቋልና በብዛት ሸቀት የሚጠቀምም የለም፡፡ እንደሚታወቀው ከተፈናቀልን 3 ዓመት እንደመሆኑ አሁን ሽንኩርት እንኳ 250 ብር ነው ገዝተን የምንጠቀመው፡፡ ጨው እንኳ አንዷን ብርጭቆ 20 ብር ነው የምንገዛው፡፡ በጣም ውድ ነው” ብለዋል፡፡ አስተያየት ሰጪው ከላይ ከፌዴራል ጀምሮ ለህዝብም ሆነ ለእቃ ጫኝ ተሽከርካሪዎች የፀጥታ ስጋቱ አስቸጋሪ እንደመሆኑ ጉዞዎች ፈታኝ ናቸውም ነው የተባለው፡፡ነቀምቴ የእንቅስቃሴ ዕገዳ እና የህዝቡ ምሬት

ሌላው አስተያየት ሰጪያችን ስሜ አይጠቀስ ያሉ ከጅማ-አዲስ አበባ ተመላልሰው ህይወታቸውን የሚመሩ ነጋዴ ናቸው፡፡ እንደሳቸውም አስተያየት ምንም እንኳ እሳቸው የሚኖሩበት ጅማ ዞን ፍጹም ሰላም የሰፈነበት መሆኑን ብያስረዱም መንገድ ላይ ግን በብርቱ እንደሚፈተኑ ነው የሚያስገነዝቡት፡፡ “በቅርቡ አሁን በቱሉቦሎ አከባቢ በተፈጠረው የመንገድ ላይ ጸጥታ ችግር አንድ ጓደኛችን ሞቷል፡፡ ያ ደግሞ ተሸከርካሪዎችን እንደ ልብ ለማንቀሳቀስ ስጋትን ፈጥሯል፡፡ አሁን በቅርብ ቀን ግን እየሄዱ ነው፤ አንጻራዊ ሰላም ያለ ይመስላል” ነው ያሉት፡፡

“የትራንስፖርት ፈተናው ምርትን ወደ መሃል አገር ማጓጓዝንም ይፈትናል”

ከምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቲን ወረዳ አስተያየታቸውን የሰጡን በግብርና የሚተዳደሩ አስተያየት ሰጪ ደግሞ ያመረቱትን ምርት ወደ መሃል አገር ወስደው ለመሸጥ የመንገድ ላይ ደህንነቱ ፍጹም አስተማማን አለመሆኑ ግራ እንዳጋባቸው ነው የሚያስረዱት፡፡ ስሜ ይቆ ያሉን እኚህ አስተያየት ሰጪም፤ በታጣቂዎቹ ከታወጀው የአንቅስቃሴ ገደብ ከመጠናቀቁም በኋላ የመንገድ ላይ የትራንስፖርት ፍሰቱ በአስቸጋሪነቱ እንደቀጠለ ነው፡፡ “ያው መጀመሪያ “ሸነ” የእንቅስቃሴ ገደብ አወጀ፡፡ ያ ሲፈታ ደግሞ መንግስት ማን ቁሙ አላችሁ ብሎ እየቀጣ ነው፡፡ ቅጣቱን እስካልከፈሉ እንዳይንቀሳቀሱም ተደርጓል፡፡ ይህ የህዝብ ማመላለሻን ጨምሮ ሁሉም ተሽከርካሪዎችን እየፈተነ ነው አሁን” ብለዋል፡፡“የአንቅስቀሰሴ ገደብ” በኦሮሚያ ክልል

ጊዳ አያና እና ጉቲን የተባሉ እኚህ አከባቢዎች በምርት በተለይም በበቆሎ ምርት እንደሚታወቁ አስተያየት ሰጪያን አክለው ገልጸዋል፡፡ በዚህ ዓመትም እጅግ መልካም ያሉትን ይህን ምርት ከሰበሰቡ በኋላ ምርቱን ወደ ሌላ ቦታ ማጓጓዙ ፈተና መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡ “ዘንድሮ እኛ ጋ አዝመራው ከመጠን በላ ነው፡፡ ይህን ወደ ሌላ ቦታ ላለመስደድ ነው መንገዱ የሚስተጓጎለው” የሚል መላምታቸውንም ገልጸዋል፡፡

ዶይቼ ቬለ ስለነዋሪዎቹ ስጋት እና እልባቱ ተጨማሪ መረጃዎችን ከመንግስት ለማረጋገጥ ለክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ብደውልም ስልካቸው ባለመነሳቱ አስተያየታቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡፡የተነቃቃችው ጅማ በኦሮሚያ ክልል የሰላም ደሴት

ከሁለት ሳምንታት ገደማ በፊት ግን በክልሉ በሚገኙ ታጣቂዎች ተጠርቷል የተባለው የእንቅስቃሴ ገደብ ግን በአንዳንድ የክልሉ አውራ ጎዳናዎች ላይ ተሽከርካሪዎች መንገድ ላይ ቀንሰው ከመስተዋላቸውም ባለፈ በእንቅስቃሴ ገደቡ የበርካቶች ህይወት መፈተኑ ተዘግቦ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

እሸቴ በቀለ