1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ህልሟን እውን ለማድረግ የተቃረበች እጩ ሴት አብራሪ

እሑድ፣ መጋቢት 1 2016

ቤተልሔም አካሉ ትባላለች፡፡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪየሽን ዩኒቨርሲቲ የፓይለት ስልጠና ትምህርት ቤት እጩ አብራሪ ናት፡፡ ካፕቴን (ፓይለት) ሆና ግዙፍ አውሮፕላኖችን በተለያዩ ዓለማት ማብረርን ህልሟ አድርጋ እየተጋች ያለች ወጣት ናት፡፡

https://p.dw.com/p/4dMYG
Äthiopien Assistenz Pilotein Bethelihem Akalu am Frauentag
ዕጩ አብራሪ ብተልሄም አካሉ ምስል Seyoum Getu/DW

ህልሟን ለመኖር የተቃረበችው ዕጩ አውሮፕላን አብራሪ

ህልሟን እውን ለማድረግ የተቃረበች እጩ ሴት አብራሪ

ቤተልሔም አካሉ ትባላለች፡፡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪየሽን ዩኒቨርሲቲ የፓይለት ስልጠና ትምህርት ቤት እጩ አብራሪ ናት፡፡ ካፕቴን (ፓይለት) ሆና ግዙፍ አውሮፕላኖችን በተለያዩ ዓለማት ማብረርን ህልሟ አድርጋ እየተጋች ያለች ወጣት ናት፡፡ ሙያው በብዛት ወንዶች የተካኑበት ቢሰኝም አሁን አሁን ዓርዓያ እየሆኑ የመጡ ሴት አብራሪዎች ተምሳሌት ሆነው ሙያው የሴት ልጅም ልታሳካው የሚችል መሆኑን እየሳዩን ነው ስትል ትሞግታለች፡፡ “በርግጥ ሙያውን ወንዶች ተቆጣጥረውት ቢቆዩም የወንዶች ብቻ ሙያ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ሙያው በሴቶችም የሚሰራ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ገብተው ስኬታማ የሆኑ የምናውቃቸው ሴቶች አሉ፡፡ እኔም አስቀድሞ በውስጤ ያለ ፍላጎት በመሆኑ እድሉን ሳገኝ እንደማሳካው እርግጠኛ ሆኜ ነው ወደዚህ ሙያ የመጣሁት” ትላለች፡፡ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ገንዘብ ወይስ ጥረት?

ለአብራሪነት መስፈርቱ ምንድነው?

ቤቴልሔም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካል እና ከኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪዋን አጠናቃ ነው ወደ አቪየሽን ዩኒቨርሲቲው በመምጣት የፓይለትነት ህልሟን ለማሳካት የምትታትረው፡፡ የመመሪያ መስፈርት የሆነውን የመጀመሪያ ዲግሪ በተዛማች ዘርፍ ተምሮ ማጠናቀቅ ነው የምትለው እጩ ፓይሌቷ፤ ሙያው ለሁሉም ካስቀመጠው መስፈርት ውጪ ወንድ-ሴት ብሎ የሚለየው የለውም ስትልም ታስረዳለች፡፡አርአያ ያለዉ ምግባር ለፈፀሙ የዶይቼ-ቬለ ማበረታቻ “ለወንዶች አሊያም ለሴቶች ብሎ ለብቻ የተጻፈ መስፈርት የለም፡፡ ከዚህ በፊት እህቶቻችን የሚፈተኑበት አትችይውም ይህ ከባድ ነው የሚል ፈተናም እኔም አላጋጠመኝም፡፡ በርግጥ እዚህ ለመግባት ለሁሉም ሰው ፈተናው ዘርፈ ብዙና ከባድ ነው፡፡ ከጠነከርን ግን ሁሉም ይቻላል ብየ ነው ጠንክሬ የምሰራው” ብላለች፡፡

ቤቴልሔም ወደ አውሮፕላን አብራሪነት የሚወስደውን ሙያ በየደረጃው እየቀሰመች መሆኑንም ስታስረዳ፤ “በስልጣነው ትምህርት ቤት መጀመሪያ ገራውንድ ትምህርት አለ፡፡ በዚያ የንድፍ ትምህርት በስፋት ይሰጣል፡፡ ከዚያ በኋላ ነው በትግባር ላይ የተመሰረተ የበረራ ትምህርት የሚመጣው፡፡ በዚህ ወደ አምስት ደረጃዎች አሉ፡፡ ያንን ስናጠናቅቅ ነው ወደ አብራሪነት የምንመጣው፡፡ ስለዚህ ያንን በብቃት ማጠናቀቅ ያስፈልጋል” ትላለች፡፡በፈጠራ ስራዎቹ ወደ ቢሊነርነት እያመራ ያለው ወጣት ኢዘዲን ካሚል

“የፈጣሪ ፍቃድ ብሆን በሚቀጥለው ዓመት ፓሌት ሆኜ እንገናኛለን”

የወደፊት አብራሪዋ ቤቴልሔም ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በዋና አብራሪነት በሙያ ዘርፍ ተሰማርታ እራሷን እንደምታገኝ ትተማመናለች፡፡ “አሁን በፓይሌት ትምህርት ቤት ውስጥ ወደ አንድ ዓመት ከሁለት ወር ሆኖኛል፡፡ ትምህርቶቹን ወደ ማጠናቀቁ ነኝ፡፡ ካሁን ወዲያ የሚቀረኝ የበረራ ኦፕሬሸሽን ዝግጅት ነው፡፡ በቀጣይ ዓመት እያበረረርኩ እንገናኛለን የሚል ተስፋ አለኝ” ብላለች፡፡

በኢትዮጵያ አየር መንገድ በሴቶች ብቻ የሚመራ በረራ

በጎርጎሳውያኑ መጋቢት 08 የሚከበረውን ዓለማቀፍ የሴቶች ቀንን ምክኒያት በማድረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ የዘመናዊ A350 ኤርባስ አውሮፕላን በረራውን ወደ ለንደን ሂዝሮው እንዲያቀና አድርጓል፡፡ በዚህም ከአብራሪነት እስከ ቴክኒክ ስራዎች በሙሉ ሴቶች ብቻ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ስለዚህ ተግባር አስፈላጊነት ሲያስረዱ “ከአውሮፕላን ፍተሸ እስከ አብራሪነት ሁሉም የበረራው ስራ ላይ ሴቶች ብቻ ተሳታፊ ሆናሉ፡፡ ይህም የአቪየሽን ስራውን ሴቶች እድሉን ካገኙ እንደሚሰሩት ለማረጋገትና ለማበረታታት ነው” ይላሉ፡፡አርአያ እና ሁለገብ የሙዚቃ ሰው ፤ አደም መሐመድ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የስራ ክፍሎች አጠቃላይ የሴቶች ተሳትፎ 38 በመቶ ላይ እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡ ይሁንና ለወንዶች ብቻ በተለምዶ ሲሰጡ የቆዩት እንደ አብራሪነት እና የቴክኒሺያን የሙያ ዘርፍ ላይ አሁንም ሰፊ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ስራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ያስረዳሉ፡፡ “ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በነዚህም ሙያ በርካታ ሴቶች ድርጅቱን ተቀላቅለው በማገልገል ላይ ናቸው፡፡ ባሁን ሰዓት ከ50 በላይ ሴት አብራሪዎች አሉን፡፡ የቴክኒሺያን ስራ የጉልበት ስራ ብሆንም ወደ 150 ሴቶች በዚያ ዉስጥ ገብተው እየሰሩ ይገኛሉ” ብለዋል፡፡ አየር መንገዱ እኩል እድል በመስጠት ይህንንም የማሳደግ ውጥን መያዙን አስገንዝበዋልም፡፡

ስዬም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ