እንቦጭን ለማስወድ የጢንዚዛዎች ሙከራ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 10.07.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

  እንቦጭን ለማስወድ የጢንዚዛዎች ሙከራ

በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተውን እምቦጭ አረምን ማስወገድ የሚችሉ ጢንዚዛዎች እየተራቡ እንደሆነ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ። የጣና ሐይቅ ካለፉት 8 ዓመታት ጀምሮ እምቦጭ በተባለ አረም ተወርሮ ህልውናው አደጋ ላይ እንደሆነ በተለያዩ ባለሙያዎች ሲገለፅ ቆይቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:27

«አረሙን በስነህይወታዊ ዘዴ ለማስወገድ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ሃሳብ»

አረሙን ለማስወገድ በማሽንና በእጅ በመንቀል ለማቃለል ቢሞከርም የተፈለገውን ያህል ውጤት ሊገኝ አልተቻለም። አረሙን ለማስወገድ የሚመጡ ማሽኖችም ቢሆን ብዙም ውጤታማ ሳይሆኑ ለብልሽት እንደሚዳረጉ ከአማራ ክልል የአካባቢ፣ ደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
አሁን አረሙን በስነህይወታዊ ዘዴ ለማስወገድ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከአማራ ክልል የአካባቢ፣ ደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን ጋር በመተባበር አረሙን በመመገብ ሊያስወግዱ የሚችሉ ጢንዚዛዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማራባት ላይ ነው። ምርምሩን በበላይነት የሚመሩትና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰርና ተመራማሪ ዶ/ር ጌታቸው በነበሩ እንዳሉት የምርምር ውጤቱ በአፍሪካና በዓለም አገሮች በሚገኙ በእንቦጭ የተወረሩ ሐይቆችን ከችግሩ ማላቀቁን  አብራርተዋል።
ጢንዚዛውን በትክክል እምቦጩን እንዲመገብና በውስጡ እንዲራባ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ አረሙን መቆጣጠር እንደሚቻልና ጢንዚዛው ከእምቦጭ አረም ውጭም ሌላ ነገር መመገብ ስለማይችል በሰብል ላይ ምንም የሚያመጣው ተፅዕኖ እንደሌለም ዶ/ር ጌታቸው ለዶይቼ ቬለ DW ተናግረዋል።

Äthiopien Forschungsprogramm der Universität in Bahir Dar (DW/A. Mekonnen)

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰርና ተመራማሪ ዶ/ር ጌታቸው

አጠቃላይ ምርምሩ ውጤታማ መሆኑንና ወደ ተግባር መግባት እንደቀራቸው ተመራማሪው ዶ/ር ጌታቸው አብራርተዋል። የምርምር ውጤቱ በኢትዮጵያ አዲስ የሚተገበር እንዳልሆነ፣ ይልቁንም  በተለያዩ የአፍሪካና የዓለም አገሮች በሚገኙ በእንቦጭ የተወረሩ ሐይቆችን መታደጉንም አብራርተዋል። ጢንዚዛውን በትክክል እምቦጩን እንዲመገብና በውስጡ እንዲራባ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ አረሙን መቆጣጠር እንደሚቻልና ጢንዚዛው ከእምቦጭ አረም ውጭም ሌላ ነገር መመገብ ስለማይችል በሰብል ላይ ምንም የሚያመጣው ተፅዕኖ እንደሌለም ይናገራሉ፡፡

የጥንዚዛው ዕድሜ በአማካይ ከ3-4 ወራት ብቻ በመሆኑ በአፋጣኝ ወደ ትግበራ ካልተገባ ክስረት ነው የሚሉት ዶ/ር ጌታቸው የአማራ ክልል የአካባቢ፣ ደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን ሁኔታዎች እንዲመቻቹና ባፋጣኝ ወደ ሥራ የሚገባበትን ሁኔታ ሊፈጥር እንደሚገባም አሳስበዋል።

የአማራ ክልል የአካባቢ፣ ደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጋሻው እሽቱ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ጢንዚዛዎችን ተጠቅሞ በጣና ላይ የተንሰራፋውን አረም ለማስወገድ አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቅቋል ነው ያሉት። ጢንዚዛዎች አንቦጭ ቅጠሉን ለምግብነት፣ ግንዱን ደግሞ ለመራቢያነት በመጠቀም ከሐይቁ እንደሚያስወግዱት ዶ/ር ጌታቸው ከዶይቼ ቬለ DW ጋር በነበራቸው ቆይታ አመልክተዋል።

የዕለቱ የሳይንስ እና ቴኪኒዎሊጂ መሰናዶ ይህን ያስቃኛል። ከባሕር ዳር ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን አዘጋጅቶታል።

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

 

Audios and videos on the topic