1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነትና የአሜሪካኖች አስተያየት

ነጋሽ መሐመድ
ማክሰኞ፣ የካቲት 24 2018

ጦርነቱ አድማሱን አስፍቶ የሊባኖሱ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቦላሕ እስራኤል ሲመታ እስራኤል ባንፃሩ ሊባኖስን እየደበደበች ነዉ።4ኛ ቀኑን በያዘዉ ጦርነት በመቶ የሚቆጠሩ የተለያዩ ሐገራት ዜጎች ተገድለዋል።አብዛኞቹ ኢራናዉያን ናቸዉ

https://p.dw.com/p/59jrI
ከግራ ወደ ቀኝ ገዳይና ሟች።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና ቅዳሜ የተገደሉት የኢራን ላዕላይ መሪ አ,ያቶላሕ ዓሊ ኻመኔይ።
ከግራ ወደ ቀኝ ገዳይና ሟች።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና ቅዳሜ የተገደሉት የኢራን ላዕላይ መሪ አ,ያቶላሕ ዓሊ ኻመኔይ።ምስል፦ IMAGO | picture alliance

እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነትና የአሜሪካኖች አስተያየት

እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ በ8 ወራት ዉስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት መካከለኛዉ ምሥራቅን እያመሰቃቀለዉ ነዉ።ኢራን የሁለቱን ጥብቅ ወዳጆች ጥቃት ለመበቀል እስራኤልንና የዩናይትድ ስቴትስ ንብረቶች ያሉባቸዉን ሐገራት በሙሉ እየመታች ነዉ።ጦርነቱ አድማሱን አስፍቶ የሊባኖሱ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቦላሕ እስራኤል ሲመታእስራኤል ባንፃሩ ሊባኖስን እየደበደበች ነዉ።4ኛ ቀኑን በያዘዉ ጦርነት በመቶ የሚቆጠሩ የተለያዩ ሐገራት ዜጎች ተገድለዋል።አብዛኞቹ ኢራናዉያን ናቸዉ።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱ ገና መጀመሩ ነዉ ይላሉ።ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ግን አብዛኛዉ የአሜሪካ ህዝብ ጦርነቱን አይደግፍም።

አበበ ፈለቀን 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ