ኤርትራ በሰሜን ምስራቅ አፍሪቃ የምትገኝ የቀይ ባህር ዳርቻ ያለት ሀገር ነች። ከሱዳን፣ ከኢትዮጵያ እና ከጅቡቲ ጋር ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ አስመራ ነው።
ኤርትራ በጣሊያን ቅኝ አገዛዝ እና በብሪታንያ የበላይ ጠባቂነት እስከ እጎአ በ1961 ድረስ ቆይታለች። ከኢትዮጵያ ጋር መጀመሪያ በፌደረሽን ኋላ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተዋሕዳለች።የኤርትራ አማፂያን ከኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት ጋር 30 ዓመታት የፈጀ ጦርነት አድርገዉ በ1991 ጊዚያዊ፣ ከሁለት ዓመት በኋላ ሙሉ ነፃነት አዉጀዋል።