ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ኢትዮጵያ ምስራቅ አፍሪቃ ውስጥ የምትገኝ ሀገር ናት። ኤርትራ፣ ሱዳን፣ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ ፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲ ያዋስኗታል። 1.1 ሚሊዮን ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ያላት ሲሆን ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ አላት።
ኢትዮጵያ በአውሮጳ ቅኝ አገዛዝ ሥር ያልወደቀች ብቸኛዋ አፍሪቃዊት ሀገር ነች።
በዛሬው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት መሰናዶ፦ የሰሜን ሸዋው ጥቃት፤ የሲኖዶስ ሕገወጥ የጳጳሳት ሹመት የቀሰቀሰው ቁጣ እንዲሁም የአቶ በረከት ስምዖን መፈታት ላይ እናተኩራለን። አስተያየቶቻችሁ የተሰባሰበበትን ጥንቅር ሙሉ ዘገባ በድምፅ ማድመጥ ይቻላል።
አቶ ማሞ ምኅረቱ "ገንዘብ የማተምና የማሠራጨት፣ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ማስተዳደር፣ የገንዘብ ፖሊሲ የማውጣትና የመተግበር" ኃላፊነት የተሰጠውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በገዥነት ሲመሩ በርካታ ፈተናዎች ይጠብቋቸዋል። የዋጋ ንረትና የውጭ ምንዛሪ እጥረት የባንኩና የገዥውን መፍትሔ ከሚሹ መካከል ናቸው። ስለ ሹመታቸው ባለሙያዎች ምን ይላሉ?
መንግስት የሚቆጣጠረዉ ኮሚሽን አክሎ እንዳለዉ ከተፈናቃዮቹ ግምሽ ያሕሉ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችና ሕፃናት ናቸዉ።ይሁንና ኢሰመኮ አክሎ እንዳስታወቀዉ በየአካባቢዉ ስለሚፈናቀለዉ ሕዝብ በቂ መረጃ ባለመጠናቀሩ ለችግር ለተጋለጠዉ ተፈናቃይ የሰብዓዊ ድጋፎችን ለማቅረብ እንቅፋት ሆኗል።
የዩናይትድስቴትስን የውጭ ፖሊሲ የሚያዘጋጀው ዋይት ሐወስ ብቻ አይደለም። ኮንግረሱ፣መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ማህበረሰብና በውጭ የሚኖሩም ጭምር ናቸው። በቅርብ ጊዜ ዩናይትድስቴትስ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለው ፖሊሲ በርግጥ በጣም መከፋፈል የሚታይበት ነው። ዋሽንግተን ውስጥ ያለው የተወሰነ አካል ነገሮችን የሚያይበት መንገድ በጣም የተለየ ነው።"
ከ60 በላይ የኢትዮጵያ ሲቪል ማሕበራት እንዲሁም የሌሎች ተቋማት ተወካዮች ዛሬ በመቐለ ተገኝተው ከትግራይ ክልል ሲቪል ተቋማት አመራሮች ጋር ተወያዩ። የተቋማቱ የዛሬ የመቐለ ጉብኝት በጦርነቱ ምክንያት ለሁለት ዓመት ተቋርጦ የቆየ ማእከላቸው አዲስአበባ እና መቐለ ያደረጉ የሲቪል ተቋማት ግንኙነት ዳግም ያስጀመረ ተብሎለታል።
ከ1960ዎቹ ጀምሮ የሚዘከረዉ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ታሪክ፣ከ1980ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ የሚነገረዉ የኤርትራ የሐገርነት ታሪክም የሱና የሳቸዉ ሚና ካልታከለበት በርግጥ ጎደሎ ነዉ።ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ።ለኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም አኞ ጠላት ናቸዉ።ገንጣይ።ለመለስ ዜናዊ ግን መላዕክም-ሰይጣናም ብጤ ናቸዉ።
``ከመጀመሪያው እኛ ያለን አቋም TPLF በሕግ የማይገዛ፣ በውይይት የማያምን፣ ለብቻው ብቻ በስልጣን መኖር የሚፈልግ የጥቅምና የቤተሰብ ስብስብ ነው ብለን ነው የምናምነው። እና ይህ የስልጣን ነጋዴ በሃይል በስልጣን ላይ ሊቀጥል እንጂ የሽግግር መንግስት ለማቋቋም ዝግጁ እንዳልሆነ የሚያረጋግጡልን ብዙ ነገሮች አሉ። ``