1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢሰመኮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ብቻ እንዲወሰን ለመንግስት ጥሪ አቀረበ

ሰኞ፣ ነሐሴ 8 2015

የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ በአማራ ክልል በሙሉ እንዲሁም በመላው ሀገሪቱ እንደአስፈላጊነቱ ተፈጻሚ የሚሆን እና ለስድስት ወራት የሚቆየው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈጻሚነት በአማራ ክልል ብቻ እንዲገደብ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ። ፤ ኮሚሽኑ የአፈጻጸም ጊዜው ወደ አንድ ወር እንዲያጥርም ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።

https://p.dw.com/p/4V6Am
Äthiopien Menschenrechtskommission
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መስሪያ ቤትምስል Solomon Muche/DW

የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ በአማራ ክልል በሙሉ እንዲሁም በመላው ሀገሪቱ እንደአስፈላጊነቱ ተፈጻሚ የሚሆን እና ለስድስት ወራት የሚቆየው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈጻሚነት በአማራ ክልል ብቻ እንዲገደብ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ። ፤ ኮሚሽኑ ጊዜውም ወደ አንድ ወር እንዲያጥር ኢሰመኮ ምክረ ሃሳብ አቀረበ። ኮሚሽኑ ለመንግስት በላከው የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ እና ትንታኔ ዝርዝር ምክረ ሐሳቦች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጊዜው ወደ አንድ ወር እንዲያጥር ጠይቋል።

ኮሚሽኑ ለምክር ቤቱ በላከው የትንታኔ ሰነድ ላይ እንደተመለከተው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ፣ በተለይም በአዋጁ የተመለከቱ ክልከላዎችና ግዴታዎች፣ ለመንግሥት የተሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን፣ የአዋጁ ከባቢያዊና የጊዜ ተፈጻሚነት ወሰን፣ የሕዝብ ተወካዮች እና ዳኞችን ያለምክር ቤቱ ውሳኔ አለመያዝና መከሰስ ልዩ መብት (Immunity) ጨምሮ ሌሎችም ሊገደቡ ስለማይችሉ መብቶች ጥበቃ፤ በአጠቃላይ የአዋጁ እያንዳንዱ አንቀጾች ከጥብቅ አስፈላጊነት (necessity)፣ ተመጣጣኝነት (proportionality) እና ሕጋዊነት (legality) አንጻር አንዲመረመሩ ይጠይቃል፡፡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ እዝም ተቋቁሞለት እየተተገበረ ያለው አዋጁ ምን ያህል አሳሳቢ ሆኖ ነው ኢሰመኮ ማሳሰቢውን ያወጣ በሚል የተጠየቁት፤ በኮሚሽኑ የሰብዓዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ክፍል ዋና ኃላፊ ዶ/ር ሚዛኔ አባቴ ለዶቼ ቬለ በሰጠት ተጨማሪ ማብራሪያ የአዋጁ ተፈጻሚነት ከሰብዓዊ መብት ጥበቃ አንጻር የሚያደርሰውን ጫና ለመቀነስ ታስቦ ነው የሚል ምላሸሽ ሰጥተውናል፡፡ “ኢሰመኮ ማሻሻያ ካደረገ በኋላ ከኮቪድ ጊዜ እና በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጊዜ ሁለት ጊዜ የአዋጁ መታወጅ ያስከተላቸው የሰብዓዊ መብት ጫና ላይ ልምድ ስለቀሰምን አሁንም ሊደርስ የሚችለውን ጫና ለመቀነስ በማሰብና በመደበኛ የህግ አሰራር ሊፈቱ የሚችሉ ጉዳዮችም ካሉ ምክር ቤቱ እንዲያጠነው ለማሳሰብ ነው” ሲሉም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡የአማራ ክልል ቀውስ፦ ገፊ ምክንያቶች፣ ዳፋው እና በውይይት የመቋጨት ተስፋ

ኮሚሽኑ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጁን አስመልክቶ አዋጁ በተነገረበት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ባወጣው መግለጫ፣ በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ሰብአዊ መብቶች ሊከበሩ እንደሚገባ አሳስቦ፤ በተለይም ከሚያዝያ ወር 2015 ዓ.ም. በአማራ ክልል እየተባባሰ ለመጣው የትጥቅ ግጭት እና የጸጥታ ችግር ዘላቂ እና ሰላማዊ መፍትሔ የማፈላለግ ጥረት እንዲቀድም ጥሪ ማቅረቡንም በመግለጫው አስታውሷል። ኮሚሽኑ ከሚያደርገው መደበኛ የሰብአዊ መብቶች ክትትል በተጨማሪም በተለይ በአስቸኳይ ጊዜ ወቅት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን ክትትል እንዲያደርግ በማቋቋሚያ አዋጁ ሥልጣንና ኃላፊነት የተሰጠው በመሆኑ የአዋጁን አፈጻጸም በሕገ መንግሥቱና ኢትዮጵያ ተቀብላ ባጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት በማናቸውም ሁኔታ የማይገደቡ መብቶችን የመጠበቀ፣ የተመጣጣኝነት እና ከመድልዎ ነጻ መሆን መርሖችን ባከበረ መልኩ መተግበራቸውን በመከታጫ አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በነበሩት ተከታታይ ቀኖች በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ተከስቶ የነበረው የሰላምና ደህንነት ልዩ አደጋ በአሁኑ ወቅት ተወግዶና መደበኛ እንቅስቃሴዎች ወደ ነበሩበት ሁኔታ መመለስ መጀመራቸው በመንግሥት በይፋ የተገለጸ በመሆኑ፤ ምክር ቤቱ በአሁኑ ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን አስፈላጊነት፣ ከባቢያዊና የጊዜ ተፈጻሚነት ወሰንን በተለይ በጥንቃቄ በማጤን ምክር ቤቱ አዋጁን የሚያጸድቀው ቢሆን የጊዜ ተፈጻሚነቱ ከአንድ ወር ወይም የተወሰኑ ሳምንታት የበለጠ እንዳይሆንና ከባቢያዊ ተፈጻሚነቱም ልዩ አደጋው ተከስቷል በተባለበት ቦታ ብቻ የተገደበ እንጂ በጠቅላላ ሀገሪቱ እንዳይደረግ ኮሚሽኑ በምክረ ሐሳብ ጠይቋልም፡፡ ስለዚህም ምክረ ሃሳብ አስፈላጊነት የተጠየቁት ዶ/ር ሚዛኔ ሁለት መሰረታዊ ዓላማ ያለው ነው ብለዋል፡፡ “አንደኛው አዋጁ ተፈጻሚ የሚሆንበት ቦታ ሲሆን ሁለተኛው አዋጁ ተፈጻሚ የሚሆንበትን ጊዜ የሚመለከት ነው፡፡ ከቦታው አንጻር አሁን የጸጥታ መደፍረስ አጋትሞታል ከተባለው አማራ ክልል ውጪ አዋጁን የመፈጸም አስፈላጊነት ጥያቄን ማንሳትና መንግስት የአማራ ክልሉም ጸጥታ እየተሸሻለ ነው ከማለቱ አንጻር ጊዜውን ማሳጠር ቢቻል የሚል ሃሳብን ለማስጨበጥ ነው፡፡”የአማራ ክልል ከተሞች ሰላማዊ ውሎ፣ የአውሮጳ ኅብረት የአሜሪካና አጋሮቿ መግለጫ

ኢሰመኮ በተለያዩ ወቅቶች በሀገሪቱ በከፊልም ሆነ በሀገር አቀፍ የተጣሉ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታዎች ክትትል እና ምርመራ አድርጎ፣ ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለሕዝብ ይፋ ማድረጉንም አስታውሶ፤  ከእዚህ ቀደም በነበሩ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታዎች ወቅት የተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መድረሳቸውንና ከእነዚህም ውስጥ አሳሳቢ ከነበሩ ጉዳዮች ውስጥ ኢሰብአዊ አያያዞች፣ በተለይም በጥቆማ ላይ የተመሠረቱ እስሮችን በተመለከተ የጥቆማዎቹ መነሻ የሰዎቹ የብሔር ማንነት አለመሆኑን ለማረጋገጥ እና ምክንያታዊ ጥርጣሬ ስለመኖሩ ለማጣራት በቂ ጥረት ያልተደረገባቸው በርካታ እስሮች እንደነበሩ፣ ሴቶች፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች እና በመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ላይ የደረሱ ጥሰቶችን እንደሚጨምር ማመልከቱንም አሳውቋል።የአማራ ክልል ከተሞች የሰዓት ዕላፊ ገደብና የዕለቱ እንቅስቃሴ

ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትና በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችና የሰብአዊ መብቶች መርሖች ላይ በመመሥረት ባቀረበው ትንታኔ ላይ ምክር ቤቱ አዋጁን የሚያጸድቀው ቢሆን ለትርጉም አሻሚ የሆኑና ተለጥጠው በመተግበር ተገቢ ላልሆነ አፈጻጸምና የሰብአዊ መብቶች አደጋ ሊሆኑ የሚችሉ ድንጋጌዎች ላይ ሊደረጉ የሚገባቸውን ማሻሻያዎች በዝርዝር በማቅረብ ምክረ ሐሳብ መስጠቱንም ነው ያሳወቀው፡፡መከላከያ ሰራዊት ከደብረ ታቦር ወደ አዲስ ዘመን ሄዷል

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል አሳሳሰቢ ደረጃ ላይ ደርሷል የተባለውን የጸጥታ ሁኔታ ለመቀልበስ በክልሉ እና በሌሎችም አከባቢዎች እንዳስፈላጊነቱ ፈጸማል ያለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ የፊታችን ሰኞ ደግሞ በእረፍ ላይ የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጁን እንዲያጸድቀው ጥሪ መቅረቡ ይታወቃል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዕዝ ሰሞኑን በሰጠው ተደጋጋሚ መግለጫ ግን በአማራ ክልል ትላልቅ ከተሞች ውስጥ የነበረው የጸጥታ ውጥረት አሁን ላይ አንጻራዊ መረጋጋት ማሳየቱንም ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ