አፄ ኃይለ ሥላሴ፣ ባለ «ራዕዩ» ንጉሥ | ኢትዮጵያ | DW | 09.08.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አፄ ኃይለ ሥላሴ፣ ባለ «ራዕዩ» ንጉሥ

እንደ ጎርጎሮሳዊው አቆጣጣር በ1923 ዓ/ም ኢትዮጵያ የሊግ ኦፍ ኔሸንስ በመቀላቀል ከአፍሪቃ የመጀመሪያ አገር ሆናለች። ይህ እውን የሆነው አህጉሪቱ በአውሮጳ ቅኝ አገዛዝ ስር ትገኝ በነበረበት እና ግንኙነቶችም እኩል ባልነበረበት ወቅት ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:49
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:49 ደቂቃ

አፄ ኃይለ ሥላሴ

እንደ ጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር በ1922 በአዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ ማተሚያዎች ቤቶች የኢትዮጵያ የመጀመሪያውን መደበኛ ጋዜጣን ማተም ጀመሩ። አገሪቱም ወደ ፊት እየሄደች ነበር። ከዝህ ጥንቃቄ የተሞላበት ዘመናዊ አሰራር ስርዓት ጀርባ የነበሩት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ማማ ላይ ለግማሽ ምዕተ-አመት የተቀመጡት አፄ ኃይለ ሥላሴ ነበሩ። እሳቸዉ ተፃራሪ የሆኑ ችሎታዎቸው ነበሯቸዉ፣ ለኢትዮጵያ የዘመናዊነትን መሠረት የጣሉ ባህላዊ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ።

ለአልጋ ወራሽነት የተሰየመዉና ጥልቅ ትምህርት ያገኘዉ ወጣቱ ራስ ታፍሪ አገሩ ታሪካዊ የሆነ ነገር እንድታስቀምጥ ቁርጠኝነት ነበረዉ። የንጉሠ ነገሥትነቱን ስልጣን ሙሉ በሙሉ  እንደያዙ በብዙ ማለትም በኤኖሚያዊ፤ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት የተሀድሶ ለውጥ እንዲደረግ ፈቅደዋል። 
ጀርመን የሚኖሩ የታሪክ ምሁሩ ልጅ አስፋ-ወሰን አስራተ የንጉሠ ነገስቱን የመጀመሪያ ዓመታት በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፤

«እነዛ ጊዜያት የወጣት ራሳ ተፈሪ መኮን የራዕይ ጊዜያት ነበሩ። በህን ግዜ እሱ የሁሉ ሊበራል አስተሳሰብ ተሟጋች ነበር። በወቅቱ ጓደኞቹ ብቻ አልነበሩትም። እንደዚህ ዓይነቱ የምዕራቡ ዓለም አስተሳሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ የማይፈልጉ መኳንንቶች ነበሩ።»

ይሁን እንጂ ራስ ተፈሪ ጠላቶቹን  በሩቁ በመቆጣጠር  እንደ ጎርጎሮሳዊው1930 ዓ/ም በደመቀ ስነስርዓት ንጉሠ ነገስት ኃይለ ሥላሴ ሆነው ዙፋን ያዙ። ከአንድ ዓመት በኋላ የተገደበ አቅም ቢኖራቸውም የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አቋቁመው  አዲስ ሕገ-መንግስት አስፀደቁ። ይሁን እንጅ የየንጉሠ ነገስቱ የተህድሶ እቅድ በ1935 ዓ/ም የፋሽስቱ ኢጣሊያ መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ አገሪቱን በወረረበት ጊዜ ተሰናከለ። አፄ ኃይለ ሥላሴን ለስደት የደረገዉ ይህ ወረራ ያልተጠበቀ ተፅዕኖ ነበረዉ። 

በ1936 ጄኔቨ ላይ በሊግ ኦፍ ኔሸን ተገኝተው ባደረጉት የማይረሳ ንግግር የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ወራሪዎቹን ከአገራቸዉ ለማስዉጣት እንዲተባበራቸው ተማፀኑ። ይህ ንግግራቸው እሳቸዉ በዓለም አቀፍ መድረክ  ፀረ-ፋሽስት ፣ ትልቅ መሪ መሆናቸውን በማረጋገጥ ዝና አትርፎላቸዋል።            

«ንግግራቸዉን ቀጠሉ፤ እናም እስካሁን በጆሮዬ ዉስጥ የሚመላለስ አንድ እሳቸዉ ያሉት ዓረፍተ ነገር 'በአገሬ የተሎከሰችዉ ትንሿ ክብሪት አውሮፓን እንደ ትልቅ እሳት ይዉጠዋል ። እነዚህ በእርግጥም ትንቢታዊ ቃላቶች ነበሩ።» 

ምንም እንኳን ንግግራቸው አስገራሚ ቢሆንም፤  ብሪታንያውያን አጼ ኃይለ ሥላሴ አገራቸዉ እንዲመለሱ ለመርዳት እስኪወስኑ ድረስ አምስት ዓመት ነበር ያለፈው። በ1941 ወደ አገራቸዉ ከተመለሱ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ የንግሥናውን ስርዓት ለማጠናከር ተነሳሱ። በትምህርት ዘርፍ ተሃድሶ ማድረግ ቀጠሉ፤ ኢትዮጵያንም ወደ የተባበሩት መንግስታት ወሰዷት። እሳቸዉም በስፋት በዓለም ተጉዟል። እ.ኤ.አ. በ1954 እንደ መጀመረያ የዉጭ አገር መሪ አዲስ የተመሰረተችዉን የጀርመን ፌዴራል ሪፐብሊክን ጎበኙ። ይህም በሁለቱ ሀገሮች መካከል ዘላቂ ግንኙነት እንዲፈጠር አድርጓል።  

በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ንጉሠ ነገስቱ አንጋፋ ከሚባሉ መሪዎች ደረጃ ይቆጠራሉ። በጃሜይካ አንደ ራሱን የቻለ ሃይማኖት የራስታፋርያን እንቅስቃሴ በእሳቸዉ ስብእና ዙሪያ ተመሰርቷል። በፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ውስጥ   እንደ ዋና ሃይል ፣  ለአፍሪቃ ነጻነትም እንደ ተምሳሌት ይታያሉ።

«በዛሬዉ ቀን ተረጋግተን፤ በሙሉ እምነትና ድፍረት ስለወደፊቱ እናስባለን። ዛሬ የምናስበዉ ለነፃይቱ አፍሪቃ ብቻ ሳይሆን ስለ አፍሪቃ አንድነት ነዉ።»

ይሁን እንጅ በአገር ዉስጥ በጣም አምባገነን እየሆነ መጡ። በሚያስገርም ሁኔታ ከስልጣን የተወገዱበትን መንገዶችን ያመቻቹት ራሳቸዉ ናቸዉ። በንጉሳዊ አገዛዙ አለመተማመን የተነሳ  እ.ኤ.አ በ1960 የመፈንቀለ መንግስት ሙከራ ተካሂዷል። ንጉሱ ትኩረት ያልሰጡት ማስጠንቀቂያ ነበር።

«እነዚህ ሁሉ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ጥረቶች ከአገር ውስጥ ጉዳዮች ፍላጎት ጋር አልተመጣጠኑም። ይህ የሳቸዉ የከፋ ስህተት ነበር። በአገራቸዉ ዉስጥ ነገሮች እንዳይታዩ አድርገዋል። ስለዝህ በመጨረሻ ላይ አብዮቱ ሲመጣ ኢያረጁ ከነበሩት ንጉሰ ነግስት ጋር አብረን ነበር። የመጨረሻ ጥሪ ስንጠባበቅ ነበር። ሁሉም እሳተ ጎመራ እንደሚፈነዳ ያዉቅ ነበር። ማንም ይህን ለማቆም አቅም አልነበረዉም።»

በዓለም ላይ ካሉት እጅግ ጥንታዊ የሆኑ የዘውድ አገዛዝ ስርዓቶች አንዱ ለዓመታት በቀጠለ ቀውስ ሰበብ አበቃ። መስከረም 12 ቀን 1974 ኃይለ ሥላሴ ከመንበራቸዉ ተነሱ። የቁም እስር ላይ እያሉ በሀምሌ 27 ቀን 1975 አረፉ። እድሜያቸዉም 83 ነበር። 

ጃኪ ዊልሰን/መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic